የብሪቲሽ ኮሎምቢያው አውራ ዶሮ ቁጥሮችን፣ ቀለሞችን እና ፊደሎችን መለየት በመቻሉ በጊነየስ ወርድል ሪከርድስ ተመዝግቧል
የብሪቲሽ ኮሎምቢያው አውራ ዶሮ ቁጥሮችን፣ ቀለሞችን እና ፊደሎችን መለየት በመቻሉ በጊነየስ ወርድል ሪከርድስ ተመዝግቧል።
የጋብራይኦላ ደሴት ነዋሪ የሆነችው ኢሚሊ ካሪንግተን ባለፈው አመት እንቁላል ለማምረት አስባ አምስት የሀይሊን ዶሮዎችን መግዛቷን እና ቆየት ብላ ዶሮዎቹ ቁጥር እና ፊደል እንዲለዩ ማሰልጠን መጀመሯን ትናገራለች።
"ያስለጠንኳቸው ቁጥሮችን ወይም ፊደሎችን ለይተው እንዲያወጡ ነበር። ምንም እንኳ ሌሎች በርካታ ፊደሎችን ብጨምርም፣ እንዲነሱ ያሰለጠንኳቸውን ፊደሎች ለይተው አንሰተዋል" ስትል ካሪንግተን መናገሯን ዩናይትድ ፕሬስ ኢንተርናሽናል ዘግቧል።
ካሪንግተን ሁሉም ዶሮዎቿ በአንድ ደቂቃ ውስጥ ትርኢት በማሳየት የጊነስ ወርድ ሪከርድ እንዲሞክሩ ወሰነች። ከዶሮዎቿ አንዱ የሆነው ላሲ ስድስት ቁጥሮችን፣ ፊደሎችን እና ቀለሞችን በአንድ ደቂቃ ውስጥ በመለየት አሸነፈ።
የትርኢቱ የተለየ መሆን የጊነስ ወርድ ሪከርድ አዲስ ዘርፍ እንዲፈጥር አስገድዶታል። 'ዘ ቲንኪንግ ቺክን' ወይም አሳላሳይ ዶሮ በሚለው የዩቲዩብ ቻናሏ ላይ የዶሮዎቿን ስልጠና ስታሳይ የነበረችው ካሪንግተን አዲስ ዘርፍ መፈጠሩ የላሲን ችሎታ የሚያሳይ በመሆኑ ደስተኛ መሆኗን ተናግራለች።
"ዶሮዎች የተናቁ አንስሳት ናቸው። ነገርግን ቆም ብለን ካሰብን ብልህ እንስሳት ናቸው... ሌሎችን እንስሳት ተመልከት 'ምናልባት(ዶሮዎች) የተሻሉ ናቸው ብየም አስባለሁ" ብላለች ካሪንግተን።