188 መኪኖች ደግሞ ከንብረቱ ባለቤት ተቋም ውጪ እንደቆሙ ተገልጿል
የተሽከርካሪ ኦዲት በፌደራል መንግስት ተቋማት ምን ይመስላል?
የፌደራል ዋና ኦዲተር የ2015 በጀት ዓመት የፌደራል መንግሥት ተቋማትን የበጀት ኦዲት ግኝት ሪፖርትን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቧል።
ተቋሙ በዚህ ወቅት እንደገለጸው በፌደራል የመንግስት ተቋማት ውስጥ ባሉ ተሽከርካሪዎች ዙሪያ ባደረገው የኦዲት ሪፖርት 473 መኪኖች ያለ አገልግሎት ቆመዋል ብሏል፡፡
ከነዚህ ውስጥ 85ቱ መኪኖች ሊብሬ ያልቀረበላቸው ሲሆን 188 መኪኖች ደግሞ ከባለቤቱ ተቋም ውጪ እንደቆሙ በሪፖርቱ ላይ ተጠቅሷል፡፡
እንዲሁም 16 መኪኖች ደግሞ የሞተር እና ሻንሲ ቁጥር እንደሌላቸው እና እንደተቀያየሩ አስታውቋል፡፡
ከ90 በላይ የሞተር ሳይክሎች በብልሽት ምክንያት አገልግሎት እየሰጡ አይደለም የተባለ ሲሆን 44 ሞተር ሳይክሎች ደግሞ የሰሌዳ ቁጥር የሌላቸው፣ የባለቤትነት መታወቂያ ደብተራቸው በሌላ ተቋም የሆኑ፣ የሞተር ቁልፍ የሌላቸው እና ፋይል የሌላቸው ሆነው እንደተገኙ ዋና ኦዲተር ገልጿል፡፡