የሹፌሩን ድርጊት ለፖሊስ የሚያሳውቀው አዲሱ መኪና
ተመራማሪዎች ሰው ሰራሽ አስተውሎትን ተጠቅመው ጠጥተው የሚያሽከረክሩ ሹፌሮችን ማጋለጥ ችለዋል ተብሏል
አዲሱ ግኝት በመኪናው ውስጥ የሚገጠመው ካሜራ የሹፌሩን እንቅስቃሴ ቀርጾ ከማስቀመጥ ጀምሮ ጉዳዩን ለፖሊስ ሪፖርት የሚያደርግ እንደሆነም ተገልጿል
የሹፌሩን ድርጊት ለፖሊስ የሚያሳውቀው አዲሱ መኪና
አልኮል ጠጥቶ ማሽከርከር ኢትዮጵያን ጨምሮ በመላው የዓለማች ሀገራት ለትራፊክ አደጋዎች ምክንያት መሆኑ ይታወሳል፡፡
ተመራማሪዎች ጠጥተው ለሚያሽከረክሩ ሰዎች መላ ማግኘታቸው የተገለጸ ሲሆን በተሽከርካሪው ላይ በሚገጠም የሰው ሰራሽ አስተውሎት አማካኝነት ለፖሊስ ሪፖርት የሚደረግበትን ሁኔታ ፈጥረናል ብለዋል፡፡
በላይቭ ሳይንስ የምርምር ጆርናል ላይ የወጣው መረጃ እንደሚያሳየው በተሽከርካሪው ላይ የሚገጠመው ቴክኖሎጂ የአሽከርካሪውን የፊት እና የአይን እንቅስቀሴ ተከታትሎ ከቀረጸ በኋላ ሹፌሩ አልኮል መጠጣት አለመጠጣቱን ሪፖርት ያደርጋል ተብሏል፡፡
በናይጀሪያ ለደህንነቱ የሰጋ ፓስተር ክላሽ ይዞ መስበኩ አነጋጋሪ ሆኗል
እንዲሁም ቴክኖሎጂው የሹፌሩን አቀማመጥ፣ አተነፋፈስ እና አጠቃላይ እንቅስቃሴ በመመልከት ያለ ሾፌሩ እውቅና ለፖሊስ ሪፖርት ማድረግ የሚችል ነው፡፡
በአሜሪካ በዚህ ቴክኖሎጂው ላይ በተደረገው ሙከራ ጠጥቶ ሲያሽከረክር የነበረን ሹፌር ወዲያውኑ ለፖሊስ ሪፖርት አድርጎ አሽከርካሪው በቁጥጥር ስር እንዲውል መደረጉ ተገልጿል፡፡
አዲሱ ቴክኖሎጂ ጠጥተው በሚያሽከረክሩ አሽከርካሪዎች ምክንያት የሚደርሱ የትራፊክ አደጋዎችን የሚያስቀር ይሆናልም ተብሏል፡፡