ስፖርት
በካራባኦ ካፕ ፍፃሜ ዩናይትድ ከኒውካስትል በዌምብሌይ ይፋለማሉ
የኤሪክ ቴን ሀግ ቡድን ኖቲንግሃም ፎረስትን 5 ለ 0 በማሸነፍ ለፍፃሜ መድረሱ ይታወሳል
ቀያዮቹ ሰይጣኖች ለስድስተኛ ጊዜ ዋንጫውን ለማንሳት ይጫወታሉ
የካራባኦ ካፕ ፍፃሜ ማንቸስተር ዩናይትድን ከኒውካስትል ያገናኛል።
ምሽት 1 ስአት ከ30 ላይ በዌምብሌይ ስታዲየም የሚደረገው ጨዋታ ለዩናይትድ 11ኛ የፍፃሜ ፍልሚያ ነው።
ቀያዬቹ ሰይጣኖች ኖቲንግሃም ፎረስትን 5 ለ 0 በመርታት ለፍፃሜ የደረሱ ሲሆን፥ ስድስተኛውን ዋንጫ ለማንሳት ከኒውካስትል ይፋለማል።
ሳውዛምፕተንን 3 ለ 1 በማሸነፍ ለፍፃሜ የበቃው ኒውካስትል ከአምስት አስርት አመታት በኋላ ወደ ድል ለመመለስ ብርቱ ፉክክር እንደሚያደርግ ይጠበቃል።
ኒውካስስል በ1999ኙ የኤፍ ኤካ ፍፃሜ በዩናይትድ መሸነፉ የሚታወስ ነው።
ባለፉት ስምንት የዌንብሌይ ስታዲየም ግጥሚያዎችም ሽንፈት ማስተናገዱን ጎል ስፓርት አስታውሷል።
ባለፈው ሀሙስ በኢሮፓ ሊግ ባርሴሎናን ያሸነፈው የኤሪክ ቴን ሀግ ቡድን በውድድር ዘመኑ የመጀመሪያውን ዋንጫ ለማንሳት ነው የሚጫወተው።
ለአራት ዋንጫ የሚፎካከረው ቡድን የካራቦኦ ካፕ አንስቶ የድል ሞራሉ ከፍ እንዲል የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን ብለዋል ቴን ሀግ።
ቀያዬቹ ሰይጣኖች በ2017 ሳውዛምፕተንን 3 ለ 2 በመርታት አምስተኛ የካራባኦ ዋንጫ ማንሳታቸው ይታወሳል።