ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የላኩት ልዑክ ከአፍሪካ መሪዎች ጋር በአዲስ አበባ እንደሚመክር ተገልጿል
አሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣናቷን ወደ ኢትዮጵያ መላኳን የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
አሜሪካ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ቀጣዩ እሁድ ድረስ በሚቆየው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ እንደምትሳተፍ አስታውቃለች።
ሀገሪቱ በዚህ ጉባኤ ላይ የፕሬዝዳንት ባይደን አስተዳድር ስር ያሉ ከፍተኛ ባለስልጣናትን ወደ አዲስ አበባ ልከዋል ተብሏል።
የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ረዳት አምባሳደር ጆኒ ካርሰን ፣ የግሎባል ኤድስ አስተባባሪ ጆን ንኪንጋሶንግ እና ሌሎችም ባለስልጣናት ወደ ኢትዮጵያ ከመጡት የልዑካን አባላት መካከል ዋነኞቹ ናቸው።
በአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ስብሰባ ላይ ይሳተፋል የተባለው ይህ የአሜሪካ ልዑክ ከአፍሪካ መሪዎች ጋር በምግብ ዋስትና፣ በአፍሪካ-አሜሪካ ግንኙነት እና በጤና ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚመክር የነጩ ቤተ መንግሥት ቃል አቀባይ አስታውቋል።
36ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የፊታችን ቅዳሜ እና እሁድ በአዲስ አበባ ይካሄዳል።
በህብረቱ አባል ሀገራት ውጪ ጉዳይ ሚንስትሮች የሚመራው የስራ አስፈጻሚዎች ስብሰባ ዛሬ በህብረቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ተጀምሯል።