የተፈጥሮ ካርቦን ጥልቀት በሌለው ውሃ ውስጥ
ተመራማሪዎች የአየር ንብረት ለውጥን ለመዋጋት ተፈጥሮን መሰረት ያደረጉ መፍትሄዎችን እየፈለጉ ነው
የባህር ውስጥ አረሞች በሚሞቱበት ጊዜም ቢሆን ለዘመናት ካርቦን መያዝ እና አምቆ ማቆየት እንደሚችሉ ታውቋል
በቨርጂኒያ ዩኒቨርሲቲ የተመራማሪዎች ቡድን የአየር ንብረት ለውጥን ለመዋጋት ተፈጥሮን መሰረት ያደረጉ መፍትሄዎችን እየፈለጉ ነው።
ምርምሩ ተስፋን የሚሰጡ አስገራሚ ውጤቶች ላይ ደርሷል።
ተመራማሪዎች በቨርጂኒያ ምስራቃዊ የባህር ዳርቻ በሚገኘው ጥልቀት በሌለው ጨዋማ ውሃ ውስጥ ስምንት ጫማ ርዝመት ያለው ሲሊንደር አስገብተው ምርምር አድርገዋል።
"ከታችኛው ክፍል ላይ የባህር አረም የሚመስል ነገር ስናይ በጣም ተገረምን እና አንዳንዶቹ አረሞች ወደ አንድ ሽህ ዓመት ገደማ ወደ ኋላ ወስደውናል። ይህም ቫይኪንጎች ወደ ሰሜን አሜሪካ አህጉር ከመጡበት ጊዜ ቅርብ ነው" በማለት አብራርተዋል።
የመጀመሪያዎቹ ናሙናዎች ወደ ቤተ-ሙከራ ምርመራ የመጡ ሲሆን፤ በጣም ጥሩ ዜናም ይዘዋል።
የቨርጂኒያ ዩኒቨርሲቲ የአካባቢ ሳይንስ ትምህርት ክፍል የምርምር ቡድኑ ባህር ላይ የተኙ የሳር ጉዝጓዞች ካርቦንን በቋሚነት የመሳብን ሚስጥር ፈተዋል።
እነዚህ ንጣፍ የባህር ውስጥ አረሞች በሚሞቱበት ጊዜም ቢሆን ለዘመናት ካርቦን መያዝ እና አምቆ ማቆየት እንደሚችሉ ተመራማሪዎች አስታውቀዋል።