የካርበን ልቀትን የሚገታው የብሪታንያ ቴክኖሎጂ
“ባዮኢነርጂ ዊዝ ካርበን ስቶሬጅ” የተሰኘው ቴክኖሎጂ ካርበን ወደ ከባቢ አየር እንዳይለቀቅ ያደርጋል
ቴክኖሎጂው ከካርበን የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጨት የሚያስችል ነው ተብሏል
በ2022 በአለማችን 8 ቢሊየን ቶን ከሰል ተቃጥሏል። እያንዳንዱ ሰው 1 ቶን ከሰል አቃጥሏል እንደማለት።
ይህም በምድራችን ወደ ከባቢ አየር የሚለቀቀውን የካርበን ዳይ ኦክሳይድ መጠን በእጅጉ እየጨመረ እንዲሄድ አድርጎታል።
የአለም ኢኮኖሚክ ፎረም ጥናት እንደሚያሳየው በከባቢ አየር ላይ የሚገኘው የካርበን ዳይ ኦክሳይድ መጠን በ1950ዎቹ ከነበረበት በአሁኑ ወቅት በ12 ከመቶ ጨምሯል።
የበካይ ጋዝ ልቀትን ለመቀነስ ሀገራት የተለያዩ እርምጃዎችን ለመውሰድ ጥረት እያደረጉ ቢሆንም የሚታየው ለውጥ ግን አመርቂ አይደለም።
- “በ2030 የዓለም የበካይ ጋዝ ልቀት በ43 በመቶ መቀነስ አለበት”- የኮፕ-28 ፕሬዝዳንት
- በአለም ሙቀት መጨመር በ2021 470 ቢሊየን የስራ ስአት ባክኗል - ጥናት
የብሪታንያ ተመራማሪዎች ግን የካርበን ልቀትን መቀነስ ላይ ሳይሆን ልቀትን ሙሉ በሙሉ ማስቀረት ኢላማ ያደረገ ቴክኖሎጂንን ወደ ስራ ለማስገባት እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ።
“ድራክስ” የተሰኘው የሃይል ማመንጫ ወደ ስራ ያስገባዋል የተባለው ቴክኖሎጂ “ባዮኢነርጂ ዊዝ ካርበን ስቶሬጅ” ይሰኛል።
ቴክኖሎጂው በካይ የሆነውን ጋዝ ወደ ከባቢ አየር ሳይለቀቅ ከብዝሃ ህይወት ጋር በማገናኘት የሚከማችበትን ሂደት የሚፈጥር ነው።
በዚህ ሂደትም ከብክለት የጸዳ የኤሌክትሪክ ሃይል ማግኘት እንደሚቻል ይናገራሉ።
የአለም የኢነርጂ ተቋም (አይኢኤ) መረጃ እንደሚያሳየው አለማችን ከ2030 ጀምሮ 250 ሚሊየን ቶል ካርበን ዳይ ኦክሳይድ በየአመቱ ከከባቢ አየር ላይ ካላስወገደች ፈተናዋ ከአሁኑ የበዛ ይሆናል።
አሁን ባለው አካሄድ ግን ይህን ማድረግ ከባድ ቢሆንም እንደ ብሪታንያው ካርበንን ከመለቀቅ የሚያስቆሙ ተጨማሪ ቴክኖሎጂዎች ወደ ስራ ከገቡ ችግሩን ይቀንሱታል ተብሏል።