የካርቦን ልቀትን ለመቆጣጠር ቴክኖሎጂ ሁነኛ ቦታ አለው ተባለ
የአየር ንብረት ግቦችን ለማሳከት ብሎክቼይን የመረጃ ትስስር መፍጠር ልቀትን ለመቀነስ እንደሚረዳ ተነግሯል
ብሎክቼይን በፍጥነት እያደገ ላለው የመካከለኛው ምስራቅና ሰሜን አፍሪካ ክልል ተስፋ ተጥሎበታል
የብሎክቼይን ቴክኖሎጂ በሁሉም መካከል የኃይል ልውውጥ እንዲኖር ማስቻሉ አየር ንብረትን ለመቆጣጠር ጉልፍ ስፍራ አለው ተብሏል።
በአሁኑ ጊዜ ብዙ ተመራማሪዎች የአየር ንብረት ለውጥን እና የካርቦን ልቀትን በመታገል ረገድ ብሎክቼይን ያለውን ጠቀሜታ በተለያዩ መንገዶች ያነሳሉ።
የካርቦን ልቀትን መቆጣጠር እንዲሁም ዘላቂ ኃይል እና አረንጓዴ ፋይናንስ መጠቀምን ጨምሮ ቴክኖሎጂው ጠቀሜታ አለው ተብሏል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የብሎክቼይን ቴክኖሎጂ በአሁኑ ጊዜ የታዳሽ ኃይል ምንጮች በአውታሮች ውስጥ እንዲካተቱ ለማድረግ እየተተገበረ ነው ብሏል።
በዚህም በዓለም አቀፍ የባህር ማጓጓዣ ኢንደስትሪ ውስጥ ያለውን ልቀት በመቀነስ እንዲሁም ባንኮች በፍጥነት እና በአነስተኛ ወጪ ዝውውሮችን እንዲያደርጉ ያስችላል።
አል ዐይን ኒውስ ያልተማከለ ቴክኖሎጂን ለመረጃ ማከማቻ እና ስርጭት ከሚያቀርበው እና ከሚያስተዳድረው የስዊስ ስዋርም ፋውንዴሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ግሬጎር ሳፊር ጋር ቃለ ምልልስ አድርጓል።
ግሪጎር ለአል ዐይን ኒውስ እንደተናገሩት የአየር ንብረት ለውጥን በመዋጋት ረገድ ብሎክቼይን ትልቅ ሚና ይጫወታል።
ምክንያቱም የአየር ንብረት ግቦችን ለሚያሳኩ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች ስማርት መርሃ ግብሮች ልቀትንና የኃይል ፍጆታን እንዲቀንሱ ተደርገው እንዲዘጋጁ ያስችላል ብለዋል።
የመካከለኛው ምስራቅና ሰሜን አፍሪካ ክልል በፍጥነት እያደገ ነው ያሉት ስራ አስፈጻሚው፤ ከጥቂት ዓመታት ወዲህ የተጀመረውን የብሎክቼይን ፈጠራን መጠቀም እንደሚቀጥል አጽንዖት ሰጥተዋል።
የመካከለኛው ምስራቅ እና የሰሜን አፍሪካ ክልሎች በ2022 ከማንኛውም ገበያ በበለጠ ፍጥነት እያደገ የመጣው የክሪፕቶ ገበያ ነበራቸው።