ተመራማሪዎች ካርበን ጋዝ የሚመጥ አካል ፍለጋ ላይ መሆናቸው ተገለጸ
እጸዋት እና ውሀማን አካላት ካርበን ጋዝን በመምጠጥ የሚታወቁ ቢሆኑም በቂ አይደለም ተብሏል
ኢንዱስትሪዎች ወደ ከባቢ አየር በካይ ጋዝ በመልቀቁ ቀዳሚው ዘርፍ ነው
ተመራማሪዎች ካርበን ጋዝ የሚመጥ አካል ፍለጋ ላይ መሆናቸው ተገለጸ።
የምድራችን ዋነኛ ጠላት ነው የሚባለው የሰው ልጅ በተለይም በዕለት ተዕለት በሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ምክንያት ምድራችን እየተጎዳች ትገኛለች።
ለሰው ልጅ ፍላጎት ማሳኪያ በሚል የሚጠቀማቸው የሀይል ምንጮት ከፍተኛ መጠን ያለው ካርበን ጋዝ እንዲያመነጭ ያደርጋል።
ምድር በሙቀት እና ሌሎች ምክንያቶች ጉዳቶችን እንድታስተናግድ የሚያደርገው ከባቢ አየር በየጊዜው እየጨመረ ይገኛል።
የአካባቢ ጥበቃ ተመራማሪዎችም ወደ ከባቢ አየር የሚለቀቀውን ካርበን ጋዝ ለመቀነስ ምርምሮችን በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
እጸዋት እና ውሀማ አካላት ካርበን ጋዝን በመምጠጥ ወደር የማይገኝላቸው ቢሆንም ወደ ከባቢ አየር የሚለቀቀው ጋዝ በየጊዜው መጨመሩ ተመራማሪዎች ሌላ ካርበን ጋዝ መጣጭ አካል ፍለጋ ላይ ናቸውም ተብሏል።
ተመራማሪዎቹ እየፈለጉ ያሉት ከኢንዱስትሪዎች የሚለቀቅ ጋዝ ወዲያውኑ የሚመጥ አልያም ወደ ሌላ ምርት ዋነኛው ትኩረታቸው ሆኗል።
ሌላኛው የተመራማሪዎች ትኩረት ከከባቢ አየር ያለውን ካርበን ጋዝ የሚጠቀም አካል መፈለግ ሲሆን በተለይም ከሰደድ እሳት እና መሰል አደጋዎች የሚለቀቁ ካርበን ጋዝን ለመቆጣጠር ጥረት መጀመሩ ተገልጿል።
ተመራማሪዎች ወደ ከባቢ አየር የተለቀቀ ካርበን ጋዝ መጣጭ አካል ለማግኘት እያደረጉት ያለው ጥረት እስካሁን የቀጠለ ሲሆን የመጨረሻ የሚባል መፍትሔም እንዳልተገኘ ተገልጿል።