ማላዊ የአረብ ኢምሬት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ዝግጅት ን አደነቀች
በዱባይ የሚካሄደው የኮፕ28 አየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ታሪካዊ ውሳኔ ሊተላለፍበት እንደሚችልም ተገልጿል
28ኛው ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ በአረብ ኢምሬት አስተናጋጅነት ከቀናት በኋላ ታስተናግዳለች
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በየዓመቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ያዘጋጃል።
ይህ ጉባኤ በየዓመቱ በተለያዩ አህጉራት እየተዟዟረ የሚካሄድ ሲሆን የዘንድሮው ጉባኤ በተባበሩት አረብ ኢምሬት ይዘጋጃል።
ከቀናት በኋላ በዱባይ በሚዘጋጀው በዚህ ጉባኤ ላይ የቫቲካን ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስን ጨምሮ የዓለም ሀገራት ይሳተፉበታል።
የማላዊ ተፈጥሮ ሀብት ሚንስትር ሚካኤል ኦሴ (ዶ/ር) ከአልዐይን ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ የተባበሩት አረብ ኢምሬት ለዓለም አቀፉ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ልዩ ዝግጅት ማድረጓን ተናግረዋል ።
የዓለም መሪዎች፣ የአየር ንብረት ለውጥ ባለሙያዎች፣ የአካባቢ ጥበቃ አንቂዎች እና የመብት ተቆርቋሪዎች በጉባኤው ላይ እንደሚሰተፉ ይጠበቃል።
ሚንስትሩ አክለውም በዱባይ የሚካሄደው ይህ ጉባኤ ታሪካዊ እና ምድራችንን ለዘለቃው የሚጠቅሙ ውሳኔዎች ሊወሰኑ ይችላልም ብለዋል።
በዚህ ጉባኤ ላይ በተለይም ለታዳጊ ሀገራት የገንዘብ ፈሰስ እንዲደረግ እና ሌሎች የአየር ንብረት ለውጥ እና አካባቢ ጥበቃ ስራዎችን የሚያግዝ የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግበት አሰራር ይጸድቃል ብለው እንደሚጠብቁም ሚንስትሩ ገልጸዋል።
እንዲሁም በጉባኤው ሀገራት እና ተቋማት በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ የበለጠ ትብብር እና ግንኙነት መመስረት የሚያስችሉ አሰራሮች እና ውሳኔዎች የሚወሰንበት ሊሆን እንደሚችልም ሚንስትሩ ተናግረዋል ተብሏል።