የካርበን ንግድ ምንድነው?
የካርቦን ንግድ አለምአቀፍ የካቦን ልቀትን ለመቀነስ የሚያስችል መንገድ ተደርጎ ይወሰዳል
ካርበን ትሬዲንግ የብክለት መጠናቸውን ለሚቀንሱ ኩባንያዎች ማበረታቻ በመስጠት ብክለትን መቆጣጠር የሚያስችል የገበያ ስርአት ነው
የካርበን ንግድ ምንድነው?
ካርበን ትሬዲንግ ወይም ኢሚሽን ትሬዲንግ የብክለት መጠናቸውን ለሚቀንሱ ኩባንያዎች ማበረታቻ በመስጠት ብክለትን መቆጣጠር የሚያስችል የገበያ ስርአት ነው።
ይህ እንዴት ይሰራል የሚለው በዚህ ጹሁፍ ይዘረዘራል።
ካፕ፦ የበካይ ጋዝ ልቀት መጠንን የሚቆጣጠር ተቆጣጣሪሪ ባለስልጣን ነው። በዚህ መንገድ አጠቃላይ የብክለት መጠን ለመቀነስ ያስችላል።
አሎዋንስ፦ ኩባንያዎች ወይም ሌሎች አካላት እንዲለቁ የሚፈቀድላቸው የበካይ ጋዝ መጠን ነው። ምን ያህል ነው የሚለው በካፕ የሚወሰን ይሆናል።
ትሬዲንግ፦ ከተፈቀደላቸው አሎዋንስ ወይም መጠን በታች የሚበክሉ ኩባንያዎች፣ ከተፈቀደላቸው በላይ መልቀቅ ለሚፈልጉ ኩባንያዎች የተረፋቸውን መጠን መሸጥ ይችላሉ።
ይህ ኩባንያዎች የሚያደርሱት የብክለት መጠን እንዲቀንሱ ያበረታታቸዋል።
ጥቅሞች፦
ኩባንያዎች አዋጭነቱን በማየት የብክለት መጠናቸውን መቀነስ ወይም ከሌሎች የመግዛት ምርጫ ያገኛሉ።
ከተፈቀደላቸው መጠን በታች የሚበክሉ፣ ትርፉን በመሸጥ በኢኮኖሚ ተጠቃሚ ይሆናሉ።
ካርቦን ክሬዲት፦ ኩባንያዎች እንደ ደን ልማት ወይም የታዳሽ ኃይልን በመሳሰሉ ፕሮጀክቶች ላይ ኢንቨስት በማድረግ ብድር የሚያገኙበት ስርአት ነው።
አለምአቀፍ የካርቦን ትሬዲንግ፦ ይህ ሀገራት የተፈቀደላቸውን የበካይ ጋዝ ልቀት መጠን በመሸጥ ወይም በመግዛት ብሔራዊ የልቀት ቅነሳ ግባቸውን የሚያሳኩበት በቶኪዮ ፕሮቶኮል የተዋወቀ ጽንሰ ሀሳብ ነው።
የካርቦን ንግድ አለምአቀፍ የካቦን ልቀትን ለመቀነስ የሚያስችል መንገድ ተደርጎ ይወሰዳል።