የ15 ዓመቱ ጣልያናዊ በሰራቸው ተዓምራት የፊታችን ሚያዝያ በይፋ ቅዱስ ተብሎ ሊከበር ነው
የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካርሎ አኩቲስን ታማሚዎችን ፈውሷል በሚል ከቅዱሳን አንዱ እንዲሆን መወሰኗ ይታወሳል
ሁለት የእድሜ ልክ ህመምተኞች ከታዳጊው ስርዓተ ቀብር ላይ ያለውን አፈር ተጠቅመው ተፈውሰዋል ተብሏል
የ15 ዓመቱ ጣልያናዊ በሰራቸው ተዓምራት የፊታችን ሚያዝያ በይፋ ቅዱስ ተብሎ ይከበራል ተባለ፡፡
በለንደን የተወለደው ካርሎ አኩቲስ ገና በ15 ዓመቱ ነበር በፈረንጆቹ 2006 ላይ በሳምባ ምች ህይወቱ ያለፈው፡፡
የትኛውንም ዕምነት ከማይከተሉ ቤተሰቦቹ የተወለደው አኩቲስ ገና በልጅነቱ የኮምፒውተር ሳይንስ ባለሙያ እንደነበር ተገልጿል፡፡
ይህ ታዳጊ የኮምፒውተር ሙያውን በመጠቀም የካቶሊክ ዕምነትን በማስፋፋት ብዙ አስተዋጽኦ አድርጓል የተባለ ሲሆን የፈጣሪን ህያዊነት አረጋግጫለሁ በሚል ስብከቱም በበርካቶች ይታወቃል ተብሏል፡፡
ታዳጊው ህይወቱ ካለፈ በኋላ የተቀበረበት አፈር የተጠቀሙ ታማሚዎችን ፈውሷል መባሉ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ከቅዱሳን መካከል አንዱ እንዲሆን መወሰኗን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
የአፍሪካ ካቶሊክ ጳጳሳት የሮማ ሊቀ ጳጳስ ተመሳሳይ ፆታ ጥንዶችን በተመለከተ ያወጡትን አዋጅ ውድቅ አድረጉ
በጣልያኗ አሲሲ ከተማ የሚገኘው የዚህ ታዳጊ መቃብር አፈር አንድ ኮስታሪካዊት ሴት ካለባት የዐዕምሮ ህመም እንድትፈወስ ረድቷል፡፡
እንዲሁም ሲወለድ ጀምሮ ባለበት የጣፊያ ህመም ምክንያት ምግብ መመገብ ያልቻለ አንድ ብራዚሊያዊ መፈወሱን ቤተ ክርስቲያኗ አስታውቃለች፡፡
ቤተ ክርስቲያኗ የታዳጊው መቃብር አፈር በሁለት ሰዎች ላይ የሰራውን ተዓምር ካረጋገጠች በኋላ ባሳለፍነው ግንቦት ወር ላይ በፖፕ ፍራንሲስ ሰብሳቢነት ከቅዱሳን መካከል አንዱ እንዲሆን ውሳኔ አስተላልፋ ነበር፡፡
አቡነ ፍራንሲ በቫቲካን ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ተገኝተው ቅዱስ አኩቲስ በመጪው ሚያዝያ 26 ላይ በይፋ ቅዱስነቱ ይታወጃል ሲሉ ለምዕመናን ተናግረዋል፡፡