ድመቶች በዓመት 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን እንስሳትን እንደሚገድሉ ያውቃሉ?
ከሰሞኑ ይፋ የተደረገው ጥናት እንደሚያሳየው ድመቶች በዓመት ከ2 ሺህ በላይ ዝርያዎችን ይገድላሉ
ድመቶች ከአንታርክቲካ ውጪ በሁሉም አህጉራት ይኖራሉ ተብሏል
ድመቶች በዓመት 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን እንስሳትን እንደሚገድሉ ያውቃሉ?
በሰው ልጆች ተወዳጅ ከሆኑ የቤት እንስሳት መካከል አንዷ የሆነችው ድመት በምድራችን ላይ ካሉ ገዳይ እንስሳት መካከል ዋነኛዋ ተብላለች።
ተመራማሪዎች በድመት ዙሪያ ለዓመታት ሲያደርጉት የነበረውን የጥናት ውጤት ይፋ አድርገዋል።
በአሜሪካው ኡቡርን ዩንቨርስቲ የተሰራው ይህ የጥናት እንደሚያሳየው ድመቶች በዓመት 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን እንስሳትን ይገድላሉ።
ከዚህ በተጨማሪም ድመቶች በዓመት ከሁለት ሺህ በላይ ዝርያዎችን ይገድላሉ የተባለ ሲሆን ከሌሎች እንስሳት ጋር ሲነጻጸሩ በገዳይነታቸው ሶስት ዕጥፍ ይጨምራሉ።
በአውስትራሊያ ብቻ ድመቶች 300 ሚሊዮን እንስሳት እንደሚገደሉ ዘጋርዲያን ዘግቧል።
ለአካባቢ ጥበቃ ይጠቅማሉ ተብለው ከሚታወቁት ሙካከል አዕዋፋት እና ተሳቢ እንስሳት የድመቶች ዋነኛ ኢላማ እንደሆኑ ተገልጿል።
እንደ ጀርመን ያሉ የድመትን ገዳይነት የተረዱ ሀገራት የተለያዩ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ሲሆኑ በጸደይ ወራት ድመት በቤታቸው ያላቸው ዜጎች ለሶስት ወራት ከቤት እንዳይወጡ እገዳ ጥለዋል።
በአጠቃላይ ድመቶች ዘጠኝ በመቶ የሚሆኑ አዕዋፋት፣ ስድስት በመቶ አጥቢ እንስሳት እንዲሁም አራት በመቶ ተሳቢ እንስሳት በየዓመቱ በድመቶች ይገደላሉ ተብሏል።