ቀናትን በፈጀ ጥረት 1ሺ ሜትር ጥልቀት ላይ እክል ያጋጠመውን አሳሽ በህይወት ማትረፍ ተቻለ
በቱርክ በሚገኝ ዋሻ ውስጥ አንድ ሺ ሜትር ጥልቀት ላይ ባጋጠመው ህመም ምክንያት ተመልሶ መውጣት ያልቻለውን አሜሪካ የዋሻ አሳሽ በህይወት ማትረፍ መቻሉ ተገልጿል
አሳሹን ለማውጣት ለቀናት አለምአቀፍ የነፍስ አድን ሰራ ሲሰራ ቆይቱ ዛሬ ማለዳ ማውጣት መቻሉን የቱርኩ ቱማፍ የዋሻ ፌደሬሽን አስታውቋል
በቱርክ በሚገኝ ዋሻ ውስጥ አንድ ሺ ሜትር ጥልቀት ላይ ባጋጠመው ህመም ምክንያት ተመልሶ መውጣት ያልቻለውን አሜሪካ የዋሻ አሳሽ በህይወት ማትረፍ መቻሉ ተገልጿል።
አሳሹን ለማውጣት ለቀናት አለምአቀፍ የነፍስ አድን ሰራ ሲሰራ ቆይቱ ዛሬ ማለዳ ማውጣት መቻሉን የቱርኩ ቱማፍ የዋሻ ፌደሬሽን አስታውቋል።
በቱርክ በጥልቀቱ ሶስተኛ በሆነው እና በመርሲን ቱራስ ተራራዎች በሚገኘው የሞርካ ኬቭ 1040 ሜትር ጥልቀት ላይ የጨጓራ መድማት ያጋጠመው የ40 አመቱ ማርክ ዲኪይ በአለምአቀፍ የአሰሳ ተልዕኮ ላይ ተሰማርቶ ነበር።
ዲኪይ ከዋሻው የመጨረሻ መግቢያ መውጣቱን ቱማፍ በኤክስ ወይም በቀድሞ ስሙ ትዊተር በሚባለው ማህበራዊ ሚዲያ ጽፏል።
ቱማፍ አክሎም "በዚህም መሰረት አሳሹን ከዋሻው የማውጣት ዘመቻው ተጠናቋል። ለዚህ አስተዋጽኦ ያደረጋችሁ እንኳን ደስ አላችሁ" ብሏል።
ጣሊያናዊያን የነፍስ አድን ሰራተኞች ዲኪይ ከዋሻ ከወጣ በኋላ ለምርመራ ወደ በአቅራቢያ ወደሚገኝ ጊዜያዊ የህክም ማዕከል መወሰዱን ተናግረዋል።
ቀደም ብለው በተካሄዱ የነፍስ አድን ዘመቻዎች ዲኪይ ተኝቶ በህክምና ቡድን ድጋፍ ሲደረግለት ቪዲዮዎች ያሳያሉ።