ከ1ሺ ሜትር ጥልቀት መውጣት ያልቻቸውን ግለሰብ ለማዳን የነፍስ አድን ሰራተኞች እየተጣደፉ ነው
ከሚያጠናው ዋሻ ውስጥ መውጣት ያልቻለውን ግለሰብ ለማውጣት 150 የነፍስ አድን ሰራተኞች ተሰማርተዋል
ቱማፍ እንደገለጸው ከ1ሺ 40 ሜትር ርቀት ላይ የሚሰራ የስልክ ኔትዎርክ መዘርጋቱን ገልጿል
የነፍስ አድን ሰራተኞቾ ከመሬት በታች 1ሺ ሜትር ርቀት ካለው ዋሻ ህመም ገጥሞት መውጣት ያልቻለውን አሜሪካዊ የዋሻ አጥኚ ህይወት ለማዳን እየተጣደፉ ነው ተብሏል።
ከሚያጠናው ዋሻ ውስጥ መውጣት ያልቻለውን ግለሰብ ለማውጣት 150 የነፍስ አድን ሰራተኞች መሰማራታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
የ40 አመት እድሜ ያለው ግለሰቡ በቱርክ በሚገኘው ሞርካ ዋሻ አሰሳ ለማድረግ አለምአቀፍ ተልዕኮ ይዞ ሲንቀሳቀስ የጨጓራ መድማት እንዳጋጠመው የቱርክ ቱማፍ የዋሻ ፋውንዴሽን ባወጣው መግለጫ ተናግሯል።
የቱማፍ ኃላፊ ቡሌንት ጌንክ "ክሮትስ እና ጣሊያናውያንን ጨምሮ በርካታ አለምአቀፍ ቡድኖች በሚደረገው የነፍስ አድን ስራ ላይ እየተራዱ ናቸው። ግለሰቡ 1ሺ ሜትር ጥልቀት ውስጥ ገብቷል"ብሏል።
የነፍስ አድን ስራው ረጅም ጊዜ ሊፈጅ እንደሚችል ነገርግን የዲኪይ ሁኔታ ከተሻሻለ በአጭር ጊዜ ሊጠናቀቅ እንደሚችል የተናገሩት ጌንክ አሁን ላይ ግን የዲኪያ ሁኔታ መሻሻሉን እና በራሱ መቆም መቻሉን ተናግረዋል።
ቱማፍ እንደገለጸው ከ1ሺ 40 ሜትር ርቀት ላይ የሚሰራ የስልክ ኔትዎርክ መዘርጋቱን ገልጿል።
በስፍራው ያለው የህክምና ቡድን ዲኪይን ያለስትሬቸር ማውጣት ይቻል እንደሆነ ይወስናሉ ብሏል ቱማፍ።
የነፍስ አድን ሰራተኞች በለቀቁት ቪዲዮ ላይ በጥልቀቱ ሶስተኛ ከሆነው ዋሻ(ሲንክሆል) ውጭ ባለ ቦታ የቱርክ እና የአለምአቀፍ ነፍስ በድኖች ድንኳን ተክለው ይታያሉ።