ፖለቲካ
ንግድ ባንክ በሲስተም ችግር የተቋረጠው አገልግሎት መመለሱን አስታወቀ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ባወጣው መግለጫ በትናንትናው እለት የቴክኒክ ችግር አጋጥሞት እንደነበር አስታውቋል
ሰዎች ከኤቲኤም ማሽኖች ያለገደብ ገንዝብ ማውጣታቸው እና ሲያወጡም ከሂሳበቸው ምንም ቅናሽ እንዳልታየ ባንኩ ገልጿል
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባጋጠመው የቴክኒክ ወይም የሲስተም ችግር ምክንያት የተቋረጠው አገልግሎት መመለሱን አስታወቀ።
ባንኩ ዛሬ ባወጣው መግለጫ በትናንትናው እለት የሲስተም ችግር ደርሶበት እንደነበር አስታውቋል።
ባንኩ እንደገለጸው ትናንት ምሽት ላይ በርካታ ሰዎች ከኤቲኤም ማሽኖች ያለገደብ ገንዝብ ማውጣታቸውን እና ሲያወጡም ከሂሳበቸው ምንም ቅናሽ እንዳልታየ ባንኩ ባወጣው መግለጫ ጠቅሷል።
ባንኩ ገንዘብ ሲያወጡ ነበር ያላቸው ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን እና ማጣራት እየተደረገባቸው እንደሚገኝ ገልጿል።
ባንኩ ከጥቂት ሰአታት በፊት ባወጣው መግለጫ የተቋረጠው አገልግሎት በድጋሚ መጀመሩን አስታውቋል።
ባንኩ እንደገለጸው አሁን ላይ አገልግሎት የጀመሩት ቅርጫፎቹ ሲሆኑ የሞባይል፣ የኢንተርኔት ባንኪንግ እና የሲቢኢ ብር አገልግሎቶች ለማስጀመር እየሰራ ነው።
የደረሰው የሲስተም ችግር ምን እንደሆነ ባንኩ በመግለጫው በዝርዝር አልገለጸም።
ባንክ የደረሰው የሲስተም ችግር ምን እንደሆነ ባይገለጽም የሳይበር ጥቃት አለመሆኑን ገልጿል።