የግብጽ ፖውንድ ምንዛሬ ዋጋ በገበያ እንዲወሰን ማድረጉን የሀገሪቱ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ
ከባንኩ ውሳኔ በኋላ የግብጽ መገበያያ ገንዘብ የሆነው ፖውንድ ከዶላር አንጻር ዋጋው ከፍተኛ ቅናሻ አሳይቷል።
የግብጽ ብሔራዊ ባንክ የወለድ መጠን በ600 ቤዝ ፖይንት ከፍ እንዲል እና የፓውንድ ምንዛሬ ዋጋ በነጻ በገበያ እንዲወሰን ማድረጉን በዛሬው እለት አሳታውቋል
የግብጽ ፖውንድ ምንዛሬ ዋጋ በገበያ እንዲወሰን ማድረጉን የሀገሪቱ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ።
የግብጽ ብሔራዊ ባንክ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ለማረጋጋት የወለድ መጠን በ600 ቤዝ ፖይንት ከፍ እንዲል እና የሀገሪቱ ፓውንድ ምንዛሬ ዋጋ በነጻ በገበያ እንዲወሰን ማድረጉን በዛሬው እለት አሳታውቋል።
ከባንኩ ውሳኔ በኋላ የግብጽ መገበያያ ገንዘብ የሆነው ፖውንድ ከዶላር አንጻር ዋጋው ከፍተኛ ቅናሻ አሳይቷል።
ግብጽ የአንድ ዶላር የምንዛሬ ዋጋ ከ30.85 የግብጽ ፖውንድ እንዳይበልጥ ለወራት ገድባ የነበረች ቢሆንም ወሳኔውን ተከትሎ ወደ 45 ፖውንድ መድረሱን ሮይተርስ ዘግቧል።
የገንዘብ ምንዛሬን በገበያ እንዲወሰን የማድረግ ውሳኔው ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የነበረ የኢንተርናሽናል ሞናተሪ ፈንድ (አይኤሞኤፍ ) ቁልፍ ፍላጎት ነው።
ግብጽ ቀደም ሲል የገንዘብ ምንዛሬ ዋጋ በገበያ እንዲተመን እንደምታደርግ እና ፖውንድ የሚዳከም ከሆነ ግን ወደመቆጣጠር እንደምትመለስ ስትገልጽ ነበር።
በዚህ ወቅት ግብጽ ከአረብ ኢምሬትስ ጋር የካቲት ወር መጨረሻ የተፈራረመችውን 35 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ ያለውን የኢንቨስትመንት ፕሮጀክት ጨምሮ ወደ ሀገር ውሰጥ የሚገባው የውጭ ምንዛሬ ፖውንድን ጨርሶ ከመውደቅ ይታደገዋል ብላ ተማምናለች።
ከዚህ በተጨመሪም ግብጽ አሁን ያለውን የ3 ቢሊዮን ፖውንድ የእርዳታ ፕሮግራም ለማስፋት ከአይኤምኤፍ ጋር መስማማቷን ባለስልጣናት ተናግረዋል።
ብሔራዋ ባንኩ ውሳኔውን ይፋ ካደረገ በኋላ የግብጽ አለምአቀፍ ቦንዶች ጭማሪ ያሳዩ ሲሆን የረጅም ጊዜ ቦንዶች ትልቅ ትርፍ ያገኛሉ ተብሏል።
አለምአቀፍ ኢንቨስተሮች 529 የወለድ ቤዝ ፖይነት ካላቸው ከአሜሪካ ቦንዶች የግብጽን ቦንድ ለመያዝ ያላቸው ፍላጎትም ከፈረንዶቹ ሰኔ 2021 ወዲህ ዝቅ ማለቱን ሮይተረስ የጂፒሞርጋን መረጃን ጠቅሶ ዘግቧል።
የውጭ ምንዛሬ እጥረት ከተባባሰበት ከፈረንጆቹ 2022 መጀመሪያ ጀምሮ በተደረጉ ተከታታይ የማዳከም ስራዎች ፖውንድ ከዶላር ጋር ሲነጻጸር ግማሽ ያህል ዋጋውን አጥቷል።
ባለፈው የካቲት ወር መጨረሻ ላይ አረብ ኢምሬትስ በግብጽ ሰሜን ጠረፍ አዲስ ከተማ ለመገንባት በሁለት ወራት ውስጥ 35 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስት እንደምታደርግ ማሳወቋ በጥቁር ገበያ በግብጽ ፖውንድ ላይ ያለው ጫና አቃሎታል።
የግብጽ መንግስት ለግንባታው ከታሰበው ውስጥ 10 ቢሊዮን ዶላር የሚሆነው ገቢ መደረጉን ገልጿል።