ድምጻዊ ሴሊን ዲዮንን ከመድረክ ያራቃት የማይድን ህመም ምንድን ነው?
ደምጻዊቷ ከዓመታት በኋላ በቅርቡ ወደ መድረክ እንደምትመለስ አስታውቃለች
ተወዳጇ ሴሊን ዲዮን ኤስፒኤስ በተባለ የእድሜ ልክ ህመም መጠቃቷ ተገልጿል
ድምጻዊ ሴሊን ዲዮንን ከመድረክ ያራቃት የማይድን ህመም ምንድን ነው?
ካናዳዊቷ ሴሊን ዲዮን በበርካቶች ዘንድ ተወዳጅ ድምጻዊት ናት፡፡ ለስላሳ እና ጥኡም ሙዚቃዎችን በመሞዘቅ የምትታወቀው ድምጻዊ ሴሊን ዲዮን ከፈረንጆቹ 2019 ጀምሮ በህመም ላይ ትገኛለች፡፡
የ56 ዓመቷ ድምጻዊት ሴሊን ዲዮን በተለይም አም አይ አላይቭ እና ማይ ሀርት ዊል ጎ ኦን የሚለው የታይታኒክ ፊልም ማጀቢያ ሙዚቃ በብዙዎች ከተወደዱ ሙዚቃዎች መካከል ዋነኞቹ ናቸው፡፡
በመድረክ ስራዎች በምትጫወታቸው ሙዚቃዎች ብዙ ተመልካች የነበራት ሴልዲዮን ላለፉት አራት ዓመታት ባጋጠማት ህመም ምክንት ከሙዚቃ ርቃለች፡፡
480 ሚሊዮን ዶላር ሀብት ያላት ድምጻዊት ሴሊን ከቢቢሲ ጋር ባደረገችው ቃለ መጠይቅ ያጋጠማት ለየት ያለ እና የማይድን ህመም መሆኑን ተናግራለች፡፡
እንደ ዘገባው ከሆነ ድምጻዊቷ አልፎ አልፎ በሰዎች ላይ የሚከሰት የነርቭ ህመም ሲሆን ጉዳቱን መቀነስ እንጂ ማዳን የማይቻል ነው ብላለች፡፡
ብዙ ተመልካቾ ያገኙ የዓለም ሙዚቃ ክሊፖች የትኞቹ ናቸው?
ኤስፒኤእ የሚባለው የነርቭ ህመም በተለምዶ የጡንቻዎች መኮማተር ተብሎ ሊጠራ የሚችል ነው የተባለ ሲሆን ህመሙ ከተባባሰ ሰውነት እንዳይታዘዝ እና የተለመዱ ስራዎችን እንዳንሰራ ሊያደርግ እንደሚችል የህክምና ባለሙያዎች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
ድምጻዊት ሴሊን ዲዮን ላለፉት ዓመታት ህክምና ስትከታተል መቆየቷን ገልጻ ሙሉ ለሙሉ ባትድንም ወደ ናፈቃት ሙዚቃ ስራዎቿ እንደምትመለስ ተናግራለች፡፡
“በቅርቡ ወደ ኛፈቀኝን መድረክ እመለሳለሁ፣ የላስ ቬጋስ ሙዚቃ መድረክ ናፍቆኛል፣ አድናቂዎቼም ድምጼን ይሰሙታል” ስትል ከቢቢሲ ጋር በነበራት ቃለ መጠይቅ ላይ ጠቅሳለች፡፡
በሙዚቃ ስራዎቿ በርካታ ሽልማቶችን እና አድናቆቶችን ያገኘችው ድምጻዊ ሴሊን ዲዮን ከ20 በላይ አልበሞችን ለአድማጮች ያደረሰች ሲሆን “ፎሊንግ ቱ ዩ” የሚለው አልበሟ ከ32 ሚሊዮን በላይ ሽያጭን በማግኘት ትልቁ ነው፡፡