ታዋቂዋ ሙዚቀኛ ሲሊንዲዮን በኦሎምፒክ መክፈቻ ፕሮግራም ላይ ለምታቀርበው አንድ ሙዚቃ ሁለት ሚሊየን ዶላር ሊከፈላት ነው
ለ17 አመት አብሯት ከኖረው በሽታ ማገገሟን ካሳወቀች በኋላ በግዙፍ መድረክ ላይ ስራዋን ስታቅርብ ይህ ለመጀመርያ ጊዜ ነው
ታዋቂዋ የፖፕ ሙዚቃ አቀንቃኝ ሲሊንዲዮን በኦሎምፒክ መክፈቻ ፕሮግራም ላይ ለምታቀርበው አንድ ሙዚቃ ሁለት ሚሊየን ዶላር ሊከፈላት ነው
የ56 አመቷ ተወዳጅ አቀንቃኝ ሲሊንዲዮን በዘንድሮው የፓሪስ ኦሎምፒክ መክፈቻ ላይ ስራዋን እንደምታቀርብ ተሰምቷል፡፡
ደምጻዊቷ በመድረኩ አንድ ሙዚቃ ለማቅረብ ሁለት ሚሊየን ዶላር ክፍያ እንደሚፈጸምላት ደይሊ ሜል ዘግቧል፡፡
ለ17 አመታት አብሯት የቆየው እና በሙዚቃ ህይወቷ ላይ አደጋ ደቅኖ ከነበረው በሽታ ማገገሟን ካሳወቀች በኋላ በግዙፍ መድረኮች ላይ ስራዋን እንደምታቀርብ ቃል ገብታ ነበር፡፡
ሲሊንዲዮን ከበሽታው ማገገሟ ከተሰማ ወዲህ ለመጀመርያ ጊዜ በግዙፍ መድረክ ላይ ስራዋን ስታቀርብ ይህ ለመጀመርያ ጊዜ ነው፡፡
በአሁኑ ወቅት አርብ ለምታቀርበው የመደርክ ስራ ዝግጅት በፈረንሳይ ፓሪስ የምትገኝው ሲሊንዲዮን ካጋጠማት የጤና እክል ሙሉ ለሙሉ ባትድንም በጥሩ አቋም ላይ እንደምትገኝ ነው የተሰማው፡፡
ለመጨረሻ ጊዜ በመደረክ ላይ ስራዋን ያቀረበችው በ2020 በአሜሪካ ኒው ጄርሲ ተዘጋጅቶ በነበረ ኮንሰርት ላይ ሲሆን ከዛ በኋላ በኮቪድ ምክንት በተለያዩ ከተሞች ለማቅረብ አስባው የነበረውን የኮንሰርት ስራ ሰርዛለች፡፡
በሙዚቃ ህይወቷ በርካታ ክብረወሰኖችን ማስመዝገብ የቻለችው ሲሊንድዮን በ1998 ከፍተኛ ገቢ ከሚያገኙ ሴት አርቲስቶች ቀዳሚ ነበረች። ሙዚቃዎቿ ከ200 እስከ 250 ሚሊየን ቅጅ ተሸጡውላታል፡፡
በ2017 ቢልቦርድ ስኬታማ ካናዳዊት ድምጻዊ የሚል እውቅናንም አበርክቶላታል በተጨማሪም በሙዚቃ ላበረከተችው አስተዋጽኦ ሁለት የክብር ዶክትሬት ዲግሪዎችን ከተለያዩ አለም አቀፍ ዩኒቨርስቲዎች አግኝታለች፡፡
በዘንድሮው የፓሪስ ኦሎምፒክ መክፈቻ ላይ ከሲሊንዲዮን በተጨማሪ ሌዲ ጋጋ ስራዋን እንደምታቀርብ የሚጠበቅ ሲሆን ታዋቂው የራፕ ሙዚቃ ስልት አቀንቃኝ ስኑፕ ዶግ የኦሎምፒክ ችቦ ከሚለኩሱ ታዋቂ ግለሰቦች መካከል አንዱ መሆኑ ተሰምቷል፡፡
የቀድሞው የአርስናል አሰልጣኝ አስን ቬንገር ፣ ቴሪ ሄነሪ እንዲሁም የሆሊውድ ተዋናዮቹ ሳልማ ሃያክ እና ሄሊ ቤሪ በኦሎምፒክ ችቦ ማብራት ስርአት ላይ ተሳትፎ ከሚኖራቸው ተዋቂ ግለሰቦች መካከል ይጠቀሳሉ።