ለፓሪስ ኦሎምፒክ ተሳታፊዎች ከ220 ሺህ በላይ ኮንዶም መዘጋጀቱ ተገለጸ
አዋዳዳሪው አካል 200 ሺህ የወንዶች 20 ሺህ የሴት ኮንዶሞችን እንዳሰራጨ አስታውቋል
በኦሎምፒክ ውድድሮች ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ኮንዶም መሰራጭት የጀመረው ከ26 ዓመት በፊት በሴኡል ኦሎምፒክ ነበር
ለፓሪስ ኦሎምፒክ ተሳታፊዎች ከ220 ሺህ በላይ ኮንዶም መዘጋጀቱ ተገለጸ
ከሀምሉ 19 ቀን እስከ 5 ቀን 2016 ዓ.ም የሚካሄደው የፓሪስ ኦሎምፒክ ከስፖርቱ ባሻገር ለየት ያሉ ክስተቶችን በማስተናገድ ለይ ይገኛል፡፡
ከነዚህ መካከል ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል በሚል አወዳዳሪው አካል 220 ሺህ ኮንዶሞችን እንዳሰራጨ አስታውቋል፡፡
የፓሪስ ኦሎምፒክ የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ እና አገልግሎት ጉዳይ ሀላፊው ሎረንት ዳላርድ ለፍራንስ 24 እንዳሉት 200 ሺህ የወንዶች 20 ሺህ ደግሞ የሴቶች ኮንዶሞች ተዘጋጅተዋል፡፡
ሃላፊው አክለውም "ኮንዶሞቹን ምን ያህል ሰዎች እንደሚጠቀሟቸው አናውቅም፣ ነገር ግን የሚፈልግ ካለ ግን እኛ ማቅረብ አለብን" ሲሉም ተናግረዋል፡፡
የኦሎምፒክ ሜዳሊያ አግኝተው የማያውቁ 10 ሀገራት
ኮንዶሞችን በኦሎምፒክ ውድድሮች ላይ በነጻ ማደል የተለመደ ባይሆንም ለመጀመሪያ ጊዜ በፈረንጆቹ 1988 በደቡብ ኮሪያ ሲኡል በተካሄደው ኦሎምፒክ ውድድር ላይ የተወሰነ መጠን ያላቸው ኮንዶሞች ተሰራጭተዋል፡፡
በወቅቱ ኮንዶሞቹ የተሰራጩት ስለ ኤችአይቪ ኤድስ ግንዛቤ ለመፍጠር እና ጥንቃቄ የተሞላ ወሲብን ለማበረታታት በሚል እንደተሰራጩ ተገልጿል፡፡
ከዚህ ጊዜ በኋላም በሁሉም ውድድሮች ለይ ኮንዶም ማሰራጨት እየተለመደ የመጣ ሲሆን በ2016 በብራዚል ሪዮ ኦሎምፒክ ውድድር ላይ በታሪክ ትልቅ መጠን ያለው 450 ሺህ ኮንዶሞች ተሰራጭተዋል፡፡
በፈረንሳይ አሁን ላይ የአባላዘር በሽታ የሚጠቁ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን በተለይም ቂጥኝ እና ከርክር ትልቁን ድርሻ ይይዛሉ ተብሏል፡፡