ኤች አይቪ ኤድስ እና የኦሎምፒክ ውድድር ውዝግብ
ግሬግ ሉጋኒስ የተሰኘው አሜሪካዊ ዋናተኛ የኤችአይቪ ኤድስ ህመምተኛ ቢሆንም በርካታ ሜዳሊያዎችን አሸንፏል
በውድድር መሀል የደም መፍሰስ አደጋ ያጋጠመው ዋናተኛው ውድድሩን እንዲያቋርጥ ግፊት ቢደረግበትም ውድድሩን በመጨረስ ሁለት የወርቅ ሜዳያዎችን ለሀገሩ አስገኝቷል
ኤች አይቪ ኤድስ እና የኦሎምፒክ ውድድር
የፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር ሊጀመር ጥቂት ቀናትን ብቻ መቅረቱን ተከትሎ አል-ዐይን አማርኛ በኦሎምፒክ ውድድር ታሪክ ስኬታማ እና የማይረሱ ክስተቶችን እየዳሰሰ ይገኛል፡፡
በዛሬው የኦሎምፒክ ታሪክ ዳሰሳችን አሜሪካዊው ግሬግ ሉጋኒስን የውድድር ታሪክ እንደሚከተለው እናቀርብላችኋለን፡፡
ግሬግ ሊጋኒስ አሁን ላይ የ64 ዓመት እድሜ ባለጸጋ ሲሆን በዋና ስፖርት ስኬታማ ከሆኑ የዓለማችን አትሌቶች መካከል አንዱ ነው፡፡
በ1960 የተወለደው ዋናተኛ ሉጋኒስ ለመጀመሪያ ጊዜ በ16 ዓመቱ በኦሎምፒክ ውድድር ላይ መሳተፍ የቻለ ሲሆን በካናዳ ሞንትሪያል ላይ የብር ሜዳሊያ ማግኘት ችሏል፡፡
ከአራት ዓመት በኋላ በሞስኮ ኦሎምፒክ ውድድር ለይ መካፈል ቢፈልግም በወቅቱ የአሜሪካ እና ሶቭየት ህብረት ግንኙነት ምክንያት ሳይሳተፍ ቀርቷል፡፡
እንዲሁም ሉጋኒስ በሀገሩ አሜሪካ በ1984 በተካሄደው ሎስአንጀለስ ኦሎምፒክ ውድድር ላይ በዋና ውድድር ላይ ተካፍሎ ሁለት የወርቅ ሜዳሊያ ማሸነፍ ችሏል፡፡
በኮሪያዋ ሲኡል በተካሄደው የ1988 ኦሎምፒክ ውድድር ላይ የተካፈለው ይህ አትሌት በተመሳሳይ በሁለት የዋና ውድድሮች ላይ የወርቅ ሜዳሊያ ለአሜሪካ አስገኝቷል፡፡
ይሁንና ይህ አትሌት በኤችአይቪ ኤድስ ቫይረስ መጠቃቱን የሚያሳይ ውጤት ይፋ መደረጉን ተከትሎ ከበርካቶች ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡
ሉጋኒስን ተቃውሞ የገጠመው ቫይረሱ እንደተገኘበት እያወቀ በውድድሩ ላይ መሳተፍ አልነበረበትም በሚል ሲሆን በተለይም በውድድሩ ወቅት በመዋኛው ውስጥ በተፈጠረ ግጭት ምክንያት ደም መፍሰሱ ተቃውሞውን ከፍ አድርገውበት ነበር፡፡
ለፓሪስ ኦሎምፒክ ተሳታፊዎች ከ220 ሺህ በላይ ኮንዶም መዘጋጀቱ ተገለጸ
አወዳዳሪው አካል ከውድድሩ በኋላ በሰጠው ምላሽ በውድድር መሀል የደም መፍሰስን ጨምሮ ሌሎች አደጋዎች ቢያጋጥሙ በሽታ አምጪ ቫይረስ ወደ ሌሎች አትሌቶች እንዳይተላለፍ እና ቫይረሶችን ወዲያውኑ የሚገድል ኬሚካል እንደሚጠቀም አስታውቋል፡፡
ሉጋኒስ በተሳተፈበት በዋና ውድድር ወቅትም የኤችአይቪ ኤድስ ቫይረስ ወደ ሌሎች አትሌቶች እንደማይተላለፍ በውሃው ውስጥ ያለው ኬሚካልም ወዲያውኑ ቫይረሱን ስለሚገድለው በቫይረሱ የተጠቃ አትሌት እንደሌለም በወቅቱ ተገልጿል፡፡