ፈረንሳዊው የቀድሞ አሰልጣኝ በውድድሮች መካከል ያለውን 4 ዓመታት መጠበቅ ለተጫዋቾች በጣን ረጅም ነው ብለዋል
አርሰን ዌንገር “የዓለም ዋንጫ አና የአውሮፓ ዋንጫ በየሁለት ዓመት ሊካሄደ ይገባል” ሲሉ ተናገረዋል።
የቀድሞ የአርሰናል አሰልጣኝ እና በአሁኑ ወቀት በፊፋ የዓለም አቀፍ እግር ኳስ ልማት ሃላፊ የሆኑት አርሰን ዌንገር፣ “በውድድሮች መካከል ያለውን 4 ዓመታት መጠበቅ ለተጫዋቾች በጣን ረጅም ነው” ብለዋል።
የ71 ዓመቱ ዌንገር ከዚህ ቀደም የአውሮፓ ኔሽንስ ሊግ እንዲሰረዝ መጠየቃቸው የሚታወስ ሲሆን፣ ትርጉም ያላቸው ውድድሮችን ብቻ ማዘጋጀት ይገባል ሲሉም ለቤይን ስፖርት ተናገረዋል።
የጎንዮሽ ውድድሮችን ሙሉ በሙሉ ማስቆም ያስፈላጋል ያሉም ሲሆን ፣ትርጉም ያላቸው ውድድሮች ብቻ መካሄድ እንደለባቸው የስፖርት አፍቃሪው መረዳት አለበት ብለዋል።
ዌንገር በዓለም ዋንጫ መካከል ያለውን ርዝመት ሲገልጹም ፣ “የአብዛኛው ተጫዋች እድሜ በአማካኝ 27 ወይም 28 ነው፤ የዓለም ዋንጫ ደገሞ በ4 ዓመት አንዴ ነው የሚካሄደው፤ ቀጣይ ውድድር ሲደርስ እድሜያቸው 32 ወይም 33 ይሆናል፤ ይህ ደግሞ በውድድር ላይ የመሳተፍ እና ዋንጫ የማንሳት እድላቸውን ይቀንሳል” ብለዋል።
“ለዚህም ነው የዓለም ዋንጫ በየሁለት ዓመት ልዩነት መካሄድ አለበት የምለውም” ብለዋል አርሴን ዌንገር።