በቻድ የሰአት እላፊ ገደቡ የተጣለው ፕሬዘዳንት እድሪስ ዴቢ በተገደሉበት ቀን ነበር
የቻድ ወታደራዊ ምክር ቤት የፕሬዘዳንት እድሪስ ዴቢ ሞት በኋላ ጥላው የነበረውን የሰአት እላፊ ገድብ አንስታለች፡፡
በወታደራዊ ምክርቤቱ ቃል አቀባይ አዜም በርማንዶኣ አጉና የተፈረመው ማረጋገጫ እንደሚያሳየው በወታደራዊ የሽግግር መንግስቱ የተወሰዱ እርምጃዎች የመጀመሪያ እርምጃዎችንና በመላሀገሪቱ ያለውን የጸጥታ ሁኔታ ከገመገመ በኋላ የሰአት እላፊ ገደቡ ተነስቷል፡፡
በቻድ የሰአት እላፊ ገደቡ ተጥሎ የነበረው በፈረንጆቹ ሚያዚያ 20 ነበር፡፡
የሰአት እላፊ ገደቡ የተጣለው ፕሬዘዳንት እድሪስ ዴቢ በጦር ግንባር ላይ ከአማጺያን ጋር ሲዋጉ የነበሩ ወታደሮችን እየጎበኙ ሳሉ በገደሉበት ወቅት ነው፡፡
የእድሪስ ዴቢን ሞት ተከትሎ ስልጣን የያዘው ወታደራዊ መንግስት ቃል አቀባይ እንደተናገሩት ውጊያው በካኔም መቀጠሉንና፣አሁንም ውጊያው እንደሚቀጥልና ካልሆነ አለመረጋት እንደሚፈጠር ተናግረዋል፡፡
የወታደራዊ ምክርቤቱ በ37 አመቱ በዴቢ ልጂ ማሃመት እድሪስ ዴቢ መመራት ላይ ይገናል፡፡ ውጊያው በበረሃማው ካኔም ግዛት እየተካሄደ ሲሆን ይህ ቦታ ከቻድና ዋና ከተማ ኒጃሚና 180 ኪሊሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡
አማጺያኑ በዋናነት ጎራን ከሚባሉ የጎሳ አባላት የተውጣጡ ሲሆን የአማጺ ቡድኑ ስም ፍሮንት ፎር ቸንጅና ኮንኮርድ ይሰኛል፡፡ ሮይተርስ ምንጮችን ሰቅሶ የቻድ ጦር መመታቱን ዘግቧል፡፡ ዴቢ የሞቱት መቀመጫቸውን ሊቢያ ካደረጉ አማጺያን ጋር በነበረው ዉዲያ ቆስለው ነበር፡፡