ሌላኛዋ የፓሪስ አጋር ሴኔጋል የፈረንሳይ ወታደሮች ሊሰፍሩ እንደማይገባ ተናግረዋል
ቻድ ከፈረንሳይ ጋር ያላትን ወታደራዊ ስምምነት አቋረጠች፡፡
ፈረንሳይን ጨምሮ ከምዕራባዊን ሀገራት ጋር ጥሩ ወዳጅነት የነበራት ቻድ ከፓሪስ ጋር የነበራትን ወታደራዊ ስምምነት አቋርጫለሁ ብላለች፡፡
የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጉዳዩ ዙሪያ ባወጣው ማስታወቂያ ሉዓላዊነቴን በነጻነት ለማጣጣም ከፈረንሳይ ጋር የነበረውን ወታደራዊ ትብብሮች መቋረጣቸውን ገልጿል፡፡
የቻድ አዲስ ውሳኔን ተከትሎ ፈረንሳይ በሀገሪቱ ያሰፈረቻቸውን ወታደሮች እንድታስወጣ ልትገደድ ትችላለች ተብሏል፡፡
ሌላኛዋ የፓሪስ ቁልፍ የአፍሪካ አጋር የሆነችው ሴኔጋል ፕሬዝዳንት ባሲሩ ፋዬ የፈረንሳይ ወታደሮች በሀገራቸው መስፈራቸው ተገቢ እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡
ሀገሪቱ በሴኔጋል 350 ወታደሮችን በሴኔጋል ያሰፈረች ሲሆን ፕሬዝዳንት ባሲሩ ፋዬ ፈረንሳይ ወታደሮቿ በሀገራቸው መስፈራቸውን ከመተቸታቸው ባለፈ እንዲወጡ ፍላጎት የኑራቸው አይኑራቸው አልተጠቀሰም፡፡
ፈረንሳይ ከቀድሞ ቅኝ ግዛቶቿ ጋር ያላት ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሸረሸረ ሲሆን ከኒጀር፣ ቡርኪናፋሶ እና ማሊ ተገዳ እንድትወጣ መደረጉ አይዘነጋም፡፡
የፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን መንግስት በቻድ ውሳኔ ዙሪያ እስካሁን ያሉት ነገር የለም፡፡
የናይጀሪያ ፕሬዝዳንት ሶስት ጀቶች በፈረንሳይ ታሰሩ
ፈረንሳይ በአፍሪካ ባሰፈረቻቸው ወታደሮች እና በቀጣይ ሊኖራት ስለሚችለው ግንኙነት ዙሪያ አዲስ እቅድ በማውጣት ላይ እንደሆነች ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
እንደ ዘገባው ከሆነ የፈረንሳይ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኖኤል ባሮት ከሰሞኑ የቻድ ጎረቤት በሆነችው ሱዳን ጉብኝት አድርገዋል፡፡
ፈረንሳይ በቻድ፣ ጋቦን እና ኮትዲቯር በሚኖሯት ወታደሮች ዙሪያ አዲስ እቅድ ያወጣች ቢሆንም እስካሁን ዝርዝሩ ይፋ አልተደረገም፡፡