የፋይናንስ ዘርፉን ነጻ ማድረግ ሊኖሩት የሚችሉት ችግሮች
የፋይናንስ ዘርፉ ነጻ ሲሆን በተለያዩ የቁጥጥር ተቋማት መካከል ትብብር መፍጠር ፈታኝ ይሆናል
የፋይናንስ ነጻነት ወይም ሊበራላይዜሽ ጥቂት ኩባንያዎች ገበያውን እንዲጠቀልሉ እና ውድድር እንዲቀጭጭ ያደርጋል
የፋይናንስ ዘርፉን ነጻ ማድረግ ወይም ሊበራላይዜሽን በርካታ ፈተናዎች አሉት።
ጥቂቶቹ እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል።
1) ሪስክ ማኔጅመንት
የፋይናንስ ዘርፉን ነጻ ማድረግ ላልተረጋጋ የካፒታል ፍሰት፣ ለድንገተኛ የገንዘብ መዋዠቅ እና ለፋይናንስ ቀውስ እና ለመሳሰሉት አደጋዎች የመጋለጥ እድልን ይጨምራል።
2) ሬጉላቶሪ ባላንስ
ፋይናንሱን ነጻ በማድረግ እና በመቆጣጠር መካከል ያለውን ባላንስ መጠበቅ ወሳኝ ነው። ቁጥጥሩ የሚላላ ከሆነ ለከፍተኛ አደጋ እና ለፋይናንስ አለመረጋጋት ይዳርጋል።
3) አለመመጣጠን/ኢንኢኳሊቲ
የፋይናንስ ነጻነት ለተወሰኑ ቡድኖች ወይም አካባቢዎች ብቻ በማድላት የገቢ ኢፍትሃዊነት ሊያባብስ ይችላል።
4) የገቢያ መከማቸት
የፋይናንስ ነጻነት ወይም ሊበራላይዜሽን በአንድ ቦታ ክምችት በመፍጠር ጥቂት ኩባንያዎች ገበያውን እንዲጠቀልሉ እና ውድድር እንዲቀጭጭ ያደርጋል።
5) ፋይናንሻል ኢንክሉዥን
ነጻ ማድረግ የፋይናንስ አገልግሎት የሚጨምር ቢሆንም የተገለሉ የማህበረሰብ ክፍሎች ለመድረስ ጥረት ያስፈልጋል። የተወሰኑ ቡድኖች ለመጠቀም ክልከላ ሊያጋጥማቸውም ይችላል።
6) ግሎባል ኢንተግሬሽን
ሊበራላይዜሽን ለአለምአቀፍ የኢኮኖሚ መዋዠቅ የበለጠ ተጋላጭ ያደርጋል። ከውጭ የሚመጠን የኢኮኖሚ አለመረጋጋት መቋቋም ወሳኝ ነው።
7) የፖሊሲ ኮኦርዲኔሽን/ትብብር
የፋይናንስ ዘርፉ ነጻ ሲሆን በተለያዩ የቁጥጥር ተቋማት መካከል ትብብር መፍጠር ፈታኝ ይሆናል።
እነዚህን ፈተናዎች ለመፍታት ጥንቃቄ የተሞላበት ነጻ የማድረግ ደረጃዎችን መከተል፣ ለፍትሃዊነት፣ ለአካታችነት እና ለመረጋጋት ቅድሚያ የሚሰጥ ፖሊሲ ማውጣት ያስፈልጋል።