ቁጥጥር የማይደረግበት የህዝብ ቁጥር እድገት በኢኮኖሚ ላይ የሚኖረው ተጽዕኖ
ቁጥጥር የማይደረግበት የህዝብ ቁጥር እድገት በብሔራዊ ኢኮኖሚ ላይ በርካታ አሉታዊ ተጽዕኖዎችን ያሳድራል
እያደገ የሚሄድ የህዝብ ቁጥር ባለበት ሀገር ውስጥ የሚኖር ፍትሂዊ ያልሆነ የሀብት ክፍፍል በዜጎች መካከል ያለውን የኑሮ ደረጃ ልዩነት ያሰፈዋል
ቁጥጥር የማይደረግበት የህዝብ ቁጥር እድገት በኢኮኖሚ ላይ የሚኖረው ተጽዕኖ
ቁጥጥር የማይደረግበት የህዝብ ቁጥር እድገት በብሔራዊ ኢኮኖሚ ላይ በርካታ አሉታዊ ተጽዕኖዎችን ያሳድራል።
የተወሰኑት እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል።
1) የተፈጥሮ ሀብት እጥረት
የህዝብ ቁጥር መጨመር የምግብ፣ የውሃ፣ የኃይል እና የመሳሰሉት መሰረታዊ ፍላጎቶች እጥረት እንዲከሰት ያደርጋል።
2) በመሰረተ ልማት ላይ ጫና መፍጠር
ፈጣን የህዝብ ቁጥር በሚኖርበት ጊዜ በቂ መኖሪያ ቤት፣ ትራንስፖርቴሽን እና ሌሎች አገልግሎቶችን ለማቅረብ አስቸጋሪ ነው።
3) ስራ አጥነት
በህዝብ ቁጥር መጨመር ምክንያት የሚፈጠር የሰው ኃይል ከፍተኛ የሆነ የስራ አጥነት ችግር ሊያጋጥመው ይችላል፣ ይህም ኢኮኖሚያዊ አለመረጋጋት ያስከትላል።
4) የማህበራዊ አገልግሎት ጫና
መንግሰታት እንደ ጤና እና ትምህርት የመሳሰሉ መሰረታዊ አገልግሎቶችን ለማቅረብ ያስቸግረዋል። እየጨመረ ለሚሄደው ህዝብ ቁጥር የሚመጥን ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት መስጠት አዳጋች ይሆናል።
5) የኢኮኖሚ ኢፍትሃዊነት
እያደገ የሚሄድ የህዝብ ቁጥር ባለበት ሀገር ውስጥ የሚኖር ፍትሂዊ ያልሆነ የሀብት ክፍፍል በዜጎች መካከል ያለውን የኑሮ ደረጃ ልዩነት ያሰፈዋል።