የአምናው ሻፒዮን ማንቸስተር ሲቲ ከ ሪያል ማድሪድ ተደልድሏል
የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍጻሜ ድልድል በዛሬው እለት በስዊዘርላንድ ኒዮን ከተማ ይፏ ሆኗል።
በዚህም መሰረት ከ14 አመት በኋላ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቀለው አርሰናል ከጀርመኑ ከባየር ሙኒክ ጋር ተደልድሏል።
የአምናው ሻፒዮን ማቸስተር ሲቲ ደግሞ ከስፔኑ ሪያል ማድሪድ ጋ በሩብ ፍጻው የሚፋለሙ ይሆናል።
የስፔኑ አትሌቲኮ ማድሪድ ከጀርመኑ ከቦርሲያ ዶርትመንድ ጋ የተደለደለ ሲሆን፤ የፈረንሳዩ ፒኤስ ጂ ከ ባርሴሎና መደልደሉ ታውቋል።
የሩብ ፍፃሜ መርሐ ግብር ጨዋታዎች ከሚያዚያ 1 ጀምሮ መካድ እንደሚጀምሩ የወታው መርሃ ግብር ያመለክታል።
በመርሃ ግብሩ መሰረትም የዘንድሮውየአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ በዌምብሌይ ስታዲየም እንደሚደረግ ነው የተገለጸው።
የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ከ14 አመት በፊት ያስመዘገበውን ድል በተመሳሳይ ክለብ እና የውድድር መድረክ በመድገም ለሩብ ፍጻሜ መድረሱ ይታወቃል።
በፈረንጆቹ መጋቢት 9 2010 ፖርቶን 5 ለ 0 (በደርሶ መልስ ውጤት 6 ለ 2) በማሸነፍ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ሩብ ፍጻሜውን የተቀላቀሉት መድፈኞቹ፥ በበቀደሙ ጨዋታም በኤምሬትስ የፖርቹጋሉን ክለብ በመርታት ሩብ ፍጻሜ መግባታቸውን አረጋግጠዋል።
አርሰናል ከ2010 በኋላ ለሰባት ተከታታይ አመታት በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ሩብ ፍጻሜ ለመግባት ያደረጋቸው ጥረቶች ሳይሳኩ መቅረታቸውና በ2017 በባየርሙኒክ በደርሶ መልስ 10 ለ 2 የተሸነፉበት ውጤትም በአሳፋሪነቱ ይወሳል።