12 ግብረሰናይ ድርጅቶች ብክለትን ለመቀነስ የሚውል 450 ሚሊዮን ዶላር መደቡ
በአረብ ኢምሬትስ እየተካሄደ ያለው የኮፕ28 ስብሰባ ዛሬ ሶስተኛ ቀኑን አስቆጥሯል
ድጋፉ ሀገራት ከባቢ አየርን በመበከል ከፍተኛ ድርሻ ያለውን የሚቴን ልቀት ለመቀነስ የሚያደርጉትን ጥረት ያግዛል ተብሏል
12 ግብረሰናይ ድርጅቶች ብክለትን ለመቀነስ 450 ሚሊዮን ዶላር መመደባቸውን አስታውቀዋል።
12 ግብረሰናይ ድርጅቶች በሚቀጥሉት ሶስት አመታት ሚቴን የተባለውን በካይ ጋዝ ልቀት ለመቀነስ የሚውል 450 ሚሊዮን ዶላር መመደባቸውን አስታውቀዋል።
ድርጅቶቹ እንዳስታወቁት ሀገራት ከባቢ አየርን በመበከል ከፍተኛ ድርሻ ያለውን የሚቴን ልቀትን ለመቀነስ የሚያደርጉትን ጥረት ለመደገፉ ይውላል።
ቤዞስ ኧርዝ ፈንድ፣ ብሉምበርግ ፊላንትሮፊ እና ሰኩዮ ክላይሜት ፋውንዴሽንን ጨምሮ በርካታ ግብረሰናይ ድርጅቶች ሚቴን እና ሌሎች በካይ ጋዞችን ልቀት የመቀነስ ሂደት እንዲፋጠን እንደሚረዱ ተገልጿል።
ግብረሰናይ ድርጅቶቹ ይህን ያስታወቁት በአረብ ኢምሬትስ እየተካሄደ ባለው የኮፕ28 ስብሰባ፣ አረብ ኢምሬትስ፣ ከሜሪካ እና ቻይና በርካታ አዲስ ነገሮችን ይፋ ለማድረግ እየተዘጋጁ ባለበት ወቅት ነው።
በአረብ ኢምሬትስ እየተካሄደ ያለው የኮፕ28 ስብሰባ ዛሬ ሶስተኛ ቀኑን አስቆጥሯል።
የኮፕ28 ስብሰባ ከአለም ትልቁ የአየር ንብረት ጉባኤ ሲሆን ከ198 ሀገራት የተውጣጡ ተወካዮች(መሪዎች ወይም ባለስልጣናት) እና ግብረሰናይ ድርጅቶች እየተሳተፉ ይገኛሉ።