ጎግልን ሊያጠፋ የሚችል “ቻትጂፒቲ” የተሰኘ አዲስ መተግበሪያ ተሰራ
ግጥምና ዜማ ሳይቀር በራሱ ይሰራል የተባለው አዲሱ አፕ የኦፕንአይ ኩባንያ ንብረት መሆኑ ተገልጿል
ይህ አዲስ አፕ በአንድ ሳምንት ውስጥ ከ1 ሚሊየን በላይ ደንበኞችን ማፍራት ችሏል
ጎግልን ሊያጠፋ የሚችል ቻትጂፒቲ የተሰኘ አዲስ መተግበሪያ (አፕ) ተሰራ።
በኦፕን አይ ኩባንያ የለማው ይህ ማቀላጠፊያ ወይም አፕ የአርቲፊሺያል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂን በመጠቀም አዳዲስ አገልግሎቶችን ይዞ ብቅ ብሏል።
ይህ አፕ ለዓለማችን ሰዎች አዳዲስ አገልግሎቶችን ይዞ መምጣቱ የተገለጸ ሲሆን በተለይም የጽሁፍ መልዕክቶችን በመቅረጽ በኩል እጅግ ፈጣን አገልግሎት ይሰጣል ተብሏል።
- ስለ “ሲግናል” የመልክእት መለዋወጫ መተግበሪያ ምን ያህል ያውቃሉ?
- ኢትዮጵያ ፌስቡክንና ትዊተርን በሀገራዊ የማህበራዊ ትስስር ገጽ የመተካት እቅድ እንዳላት አስታወቀች
ከዚህ በተጨማሪም ይህ አፕ ግጥምና ዘፈኖችን በአጭር ሰከንድ ውስጥ እንደሚሰራ የተገለጸ ሲሆን ጎግልን ከጥቅም ውጪ ሊያደርገው እንደሚችል ተጠቅሷል።
አዲሱ አፕ በአንድ ሳምንት ውስጥ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ደንበኞችን ያፈራ ሲሆን ከሌሎች ተመሳሳይ አፖች ጋር በሚጣጣም መልኩ መሰራቱም ተገልጿል።
የትዊተር ባለቤቱ ኢለን መስክ ከኩባንያው መስራቾች መካከል አንዱ ነው የተባለ ሲሆን ይህ አፕ ለጥያቄዎች ምላሽ መስጠት፣ የተሳሳቱ መላምቶችን ማረምና ስህተቶችን በመለየት ተወዳጅነትን አግኝቷል ተብሏል።
ከዚህ በተጨማሪም ይህ አፕ የገበያ ጽሁፎችን፣ የምስጋና ደብዳቤ እና ሌሎች ጽሁፎችን በራሱ እንደሚጽፍ ተገልጿል።
ይህ አፕ በተለይም የበይነ መረብ ሽያጭ ስራዎችን፣ መልዕክቶችን፣ ለደንበኞች ምላሽ መስጠት እና ሌሎች የማይገመቱ ተያያዥ አገልግሎቶችን ይሰጣል ተብሏል።
በአሜሪካ ሳንፍራንሲስኮ ከስምንት ዓመት በፊት የተሰራው ይህ አፕ ኢለን መስክ፣ የኦፕን አፕ ስራ አስፈጻሚ በሆኑት ሳም አልትማን ባለቤት መሆናቸው ተገልጿል።
ይህ አፕ በአጭር ጊዜ የብዙዎችን ትኩረት እንደሚስብ፣ የሴራ ትንተናዎችን እንደሚያበዛ፣ የሀሰት መረጃዎችን እንደሚያባዛና ሌሎች ጉዳቶችን ሊያደርስ እንደሚችል ሲኤንኤን ባለሙያዎችን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።