ሲግናል እስከ 2021 ድረስ 105 ሚሊየን ጊዜ ዳወንሎድ የተደረገ ሲሆን፤ በዓለም ዙሪያ 40 ሚሊየን ተጠቃሚዎች አሉት
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ “ሲግናል” የሚል መጠሪያ ያለው የመልእክት ወለዋለጫ መተግበሪያ በዓለም ዙሪያ ተቀባይነቱ እየጨመረና በበርካታ ተጠቃሚዎች ዘንድም እየተወደደ መምጣቱ ተነግሯል።
በትላልቅ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች፣ የሳይበር ደህንነት ባለሙያዎች፣ ጋዜጠኞች እና የመንግስት ባለስልጣናት ዘንድ በሚስጥራዊነቱ እና ደህንነቱ የተነሳ ተወዳጅ መሆኑ የተነገረለተ መተግበሪያው፤ በግል መረጃ መልእክት ከመለዋወጥ ጀምሮ በቡድን እስከ ማውራት የሚያስችሉ አገልግሎቶችን በውስጡ ያካተተ ነው።
ሲግናል ለምን በበርካቶች ተወዳጅ እየሆነ መጣ? ለሚለውም፤ መተግበሪያው ሙሉ በሙሉ ደህንነቱ የተጠበቀ ("end-to-end encryption") የሚቀጠም በመሆኑ ነው ተብሏል።
የስልካችን አምራች ኩብንያም ሆነ መንግስት የሚላክልንን መልእክት አግኝተው ማየት አይችሉም የተባለ ሲሆን፤ ይህም መተግበሪያው በጋዜጠኞች፣ በመንግስት ባለስልጣናት እና ሌሎችም ሚስጥራዊ መረጃን በሚለዋወጡ ሰዎች ዘንድ ተመራጭ እንዳደረገው ታውቋል።
ሲግናል ከሌሎች የመልእክት መለዋወጫ መተግበሪያዎች ጋር ተመሳሳይ የሆነ አገልግሎትን የሚሰጥ ሲሆን፤ በአይፎን፣ አንድሮይድ፣ በዊንዶውስ እና ማክ ኮምፒውተሮች ላይ በነፃ ማግኘት ይቻላል።
የአንድሮይድ ተጠቃሚዎች ከመተግበሪያው በተጨማሪም ዋነኛው የስልካችን መልእክት መላላኪያ መሆን እንደሚችልም ተውቋል።
በሲግናል መተግበሪያ ምን አይነት አገልግሎቶችን ማግኘት እንችላለን?
ሲግናል የተባለውን የመልእክት መለዋወጫ በመጠቀም የጽሁፍ መልእክት፣ የድምጽ መልእክት፣ የቪዲዮ መልእክት፣ በድምጽ እና በቪዲዮ መደዋወልን ጨምሮ የኢንተርኔት ሊንኮችን መለዋወጥ እንዲሁም ሌሎች የመልእክት መላላኪያ መተግበሪያዎች የሚሰጡትን አገልግሎቶች መጠቀም እንችላለን።
ሰዎች እንደ አጋጣሚ ስልካችንን ወስደው የተላላክነውን እንዳይመለከቱ ከሰጋን ደግሞ፤ የይለፍ ቃል አሊያም አሻራ በመጠቀም መተግበሪያውን መቆለፍ እንችላለንም ተብሏል።
በተጨማሪም የመጣልንን መልእክት ካየን በኋላ በራሱ እንዲጠፋ መድረግ የምንችል ሲሆን፤ ሌሎች ምስሎች እና ቪዲዮዎችም አንድ ጊዜ ከፍተን ካናቸው በኋላ በራሳቸው እንዲጠፉ ማደረግ ይቻላል።
ሲግናልን ለመጠቀም የግድ የስልክ ቁጥር እንደሚያስፈልገን ሲሆን፤ መተግበሪያውን ከፕሌይ ስቶር አሊያም ከአፕ ስቶር ላይ ማውረድ እንችላለን።
እንደ ፈረንጆቹ በ2018 በሚስተር ማርሊንስፓይክ የተቋቋመው ሲግናል ፋውንዴሽን፤ መጀመሪያ መነሻ በጀቱ 50 ሚሊየን ዶላር ነበር።
ሲግናል መተግበሪያ እስከ ፈረንጆቹ 2021 ድረስ 150 ሚሊየን ጊዜ ዳወንሎድ የተደረገ ሲሆን፤ አሁን ላይ በዓለም ዙሪያ ከ40 ሚሊየን በላይ ቋሚ ተጠቃዎች አሉት።