የቻትጂፒቲ ፈጣሪ ራሱን ከኒውክሌር ቦምብ ፈጣሪ ጋር ማመሳሰሉ አነጋጋሪ ሆኗል
የቻትጂፒቲ ኩባንያ የጃፓንን ከተሞች ካወደመው አቶሚክ ቦምብ ፕሮጀክት ጋር ተመሳሳይ እርምጃዎች ተከትሏል ብሏል
ኦልትማን “የሰው ሰራሽ ልህቀትን ቴክኖሎጂ በተቻለ መጠን ማሳደግ ዓላማዬ ነው” ሲል ተናግሯል
የቻትጂፒቲ አልሚና የኦፕንኤአይ የቀድሞ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሳም ኦልትማን ራሱን ከኒውክሌር ቦምብ አባት ሮበርት ኦፕንሃይመር ጋር ማገናኘቱ በፈጠራው ላይ ውዝግብ አስነስቷል።
ሳም ኦልትማን ከኒውዮርክ ታይምስ ጋር በነበረው ቃለ-ምልልስ ፈጠራውን ከኒውክሌር ቦንብ ጋር አመሳስሏል።
አሜሪካዊው የፊዚክስ ሊቅ ሮበርት ኦፕንሃይመር የኒውክሌር ቦምብ ፈጣሪ እና አባት የሚል ስም ተሰጥቷቸዋል።
ኦልትማን በቃለ ምልልሱ ላይ የአቶሚክ ቦምብ ፕሮጀክት ልዩ የማሰብ ችሎታ ካለው ቻትጂፒቲን እየገነባ ያለው ኩባንያቸው ጋር ተመሳሳይ እርምጃዎችን የተከተለ መሆኑን ተናግረዋል።
ከዚህ ቀደም ባደረጉት ቃለ ምልልስም እሳቸውና የስራ ባልደረቦቻቸው ወደፊት ሊደርሱበት የሚመኙት ደረጃ ይህ ነው ብለዋል።
ኦልትማን የኩባንያቸውን ፕሮጀክት ከኒውክሌር ቦምብ ፕሮጀክት ጋር ማነጻጸር ብቻ ሳይሆን በንግግራቸው ታዋቂ የሆኑትን የፊዚክስ ሊቅ ሮበርት ኦፔንሃይመርን ዓረፍተ ነገሮች ጠቅሰው ተናግረዋል ነው የተባለው።
ኦፕንሃይመር በ1945 ባደረጉት ታዋቂ ንግግር፤ የጃፓን ሂሮሺማ እና ናጋሳኪ ከተሞችን ለማጥፋት ያገለገለውን የመጀመሪያውን የኑክሌር ቦምብ ወግነው ተከራክረዋል።
ለቴክኖሎጂው ጊዜው መሆኑን ኦልትማን እራሳቸውን ከኦፕንሃይመር ጋር በማመሳሰል ተመሳሳይ የልደት ቀን እንደሚጋሩ ገልጸዋል።
ኦልትማን ዋና አላማቸው የሰው ሰራሽ ልህቀትን ቴክኖሎጂ በተቻለ መጠን ማሳደግ መሆኑን ተናግረዋል።