“ቻትጂፒቲ” በርካቶችን እያስደመመ ያለው አዲስ መተግበሪያ ምን የተለየ አደረገው…?
ግጥምና ዜማ ሳይቀር በራሱ ይሰራል የተባለው አዲሱ አፕ የኦፕንአይ ኩባንያ ንብረት መሆኑ ተገልጿል
አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የሚጠቀመው መተግበሪያው ሰዎችን በሚናገሩት ቋንቋ በመረዳት መልሽ መስጠት ይችላል
ባሳለፍነው ህዳር ወር ላይ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ላይ ምርምር የሚያደርገው በኦፕን አይ ኩባንያ “ቻትጂፒቲ (ChatGPT)” የተሰኘ አዲስ መተግበሪያን አስታወወቀ።
ከዚያን ጊዜ አንስቶም አዲሱ ሲስተም ኢንተርኔትን የተቆጣጠረ ሲሆን፤ አንድ ሳምንት ባለሞላ ጊዜ ውስጥ ከ1 ሚሊየን በላይ ተጠቃሚዎችን ማግኘት መቻሉም ተነግሮለታል።
በርካቶች አዲሱን አገልግሎት ከጎግል በተጨማሪ አዲስ አማራጭ እንደሆነ ምክንያቱ ደግሞ ውስብስብ ለሆኑ ችግሮች መፍትሄ የሚሰጥ በመሆኑ ነው ሲሉም ተደምጠዋል።
“ቻትጂፒቲ”GPT-3.5 የተባለ የቋንቋ ስርዓትን የሚጠቀም ሲሆን፤ ይህም ከሰዎች ቋነቋ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ጽሁፎችን እንዲጽፍ የሚያስችለው ነው ተብሏል።
“ቻትጂፒቲ” ሮቦት ዝርዝር ጽሁፎችን ጨምሮ ግጥሞችን በማዘጋጀት ችሎታው አለው የተባለ ሲሆን፤ ልዩ የሆነ የማስታወስ ችሎታ ያለው መሆኑም ነው የተነገረው።
የቦት አገልግሎቱ ከሰዎች ጋር ከዚህ በፊት ባደረገው ንግግር ውስጥ የተሰጡ አስተያየቶችን በማስታወስ ለተጠቃነሚው መልሶ የመነገር አቅም እንዳለውም ታውቋል።
ከዚህ በተጨማሪም “ቻትጂፒቲ” ግጥምና ዘፈኖችን በአጭር ሰከንድ ውስጥ እንደሚሰራ የተገለጸ ሲሆን ጎግልን ከጥቅም ውጪ ሊያደርገው እንደሚችል ተጠቅሷል።
ከዚህ በተጨማሪም ይህ አፕ የገበያ ጽሁፎችን፣ የምስጋና ደብዳቤ እና ሌሎች ጽሁፎችን በራሱ እንደሚጽፍ ተገልጿል።
ይህ አፕ በተለይም የበይነ መረብ ሽያጭ ስራዎችን፣ መልዕክቶችን፣ ለደንበኞች ምላሽ መስጠት እና ሌሎች የማይገመቱ ተያያዥ አገልግሎቶችን ይሰጣል ተብሏል።