እስረኛ የደበደበው የቺቺኑ መሪ ልጅ የአባቱ ዋና ጠባቂ ሆኖ ተሾመ
የፑቲን አጋር የሆነው ራምዛን ካዲሮቭ በወቅቱ በልጁ ድርጊት እንደሚኮራ ነበር የገለጸው
አዳም ካዲይሮቭ እስርቤት ውስጥ ሲደበድብ የሚያሳይ ቪዲዮ በአባቱ ከተለቀቀ በኋላ የተወሰኑ ወግአጥባቂ የከርሚሊን ደጋፊዎችን ጨምሮ በርካቶች አውግዘውት ነበር
እስረኛ የደበደበው የቺቺኑ መሪ ልጅ የአባቱ ዋና ጠባቂ ሆኖ ተሾመ።
በእስርቤት የነበረን ሰው ሲደበድብ የታየው የቺቺኑ መሪ ራምዛን ካዲይሮቭ የ15 አመት ልጅ አባቱን በመጠበቅ ስራ ውስጥ ከፍተኛ ሹመት ማግኘቱን የቺቺን የደህንነት ባለስልጣናት ተናግረዋል።
የቺቺኑ መሪ አጋሮች በዚህ ወር 16 አመት የሞላውን አዳም ካዲሮቭን ላሳየው ጀግንነት አድንቀዋል።
ባለፈው መስከረም ወር አዳም ካዲይሮቭ ቁርአን በማቃጠል የተከሰሰን ሰው እስርቤት ውስጥ ሲደበድብ የሚያሳይ ቪዲዮ በአባቱ ከተለቀቀ በኋላ የተወሰኑ ወግአጥባቂ የከርሚሊን ደጋፊዎችን ጨምሮ በርካቶች አውግዘውት ነበር።
የፑቲን አጋር የሆነው ራምዛን ካዲሮቭ በወቅቱ በልጁ ድርጊት እንደሚኮራ ነበር የገለጸው።
ከካይድሮቭ ከፍተኛ የደህንነት ባለስልጣናት አንዱ የሆነው ዛሚድ ቻሌቭ እንደተናገረው አዳማ የካዲይሮቭን ደህነንት የሚያረጋግጠው ዘረፍ ኃላፊ ሆኖ ተሾሙሟል።
በዚህ መሰረት አዳም የአባቱ ዋና የግል ጠባቂ ይሆናል ተብሏል።
የቺቺን የናሽናል ፖሊሲ፣ የውጭ ግንኙነት እና ፕሬስ ሚኒስትር አህመድ ዱዳይቭ በቴሌግራም መልእክታቸው በቺቺን ሪፖብሊክ የሴኩሪቲ ሰርቪስ ኃላፊ ሆኖ የተሾመውን አዳምን "እንኳን ደስ ያለህ" ብለውታል።
የሩሲያው ሪያ ኤጀንሲ እንደዘገበው ባለፈው ጥቅምት የቺቺኒያ ጀግና የሚል ሽልማት አግኝቷል።
ዱዳይቭ አዳም ካዲይሮቭ ብልህ፣ ጀግና እና ለሀይማኖቱ የሚቆም ሰው መሆኑን አስመስክሯል ብለዋል።