አቦሸማኔዎቹ ሁለት ቀን በአውሮፕላን እና በሄሊኮፕተር ከተጓዙ በኋላ 6 ስኩየር ኪ.ሜ ስፋት ባለው የፓርኩ ክፍል ተለቀዋል
ስምንት የሚሆኑ የአፍሪካ አቦሸማኔዎች ከአፍሪካዊቷ ሀገር ናሚቢያ 8 ሺ ኪ.ሜ ከተጓጓዙ በኋላ በማእከላዊ ህንድ በሚገኘው ኩኖ ብሄራዊ ፓርክ ተለቀዋል፡፡
የተወሰኑ የተፈጥሮ ኃብት ጥበቃ ባለሙያዎች ይህን ድርጊት ተችተውታል፡፡
በምድር ላይ ፈጣን የሆኑት የትልልቆቹ ድመቶች ህንድ መድረስ ከህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር 72ኛ አመት ጋር ተገጣጥሟል፤ አቦሸማኔዎቹንም ወደ ፓርኩ የለቀቋቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ናቸው፡፡ የአቦሸማኔዎቹ ወደ ፓርኩ መለቀቅ ከ70 አመታት በፊት የጠፉትን ዝርያዎች ለመተካት የተደረገው የ13 አመታት ጥረት እንዲያበቃ አድርጓል፡፡
በናሚቢያ የተካሄደው ፕሮጀክት አቦሸማኔዎች ለመጀመሪያ ጊዜ አህጉር አቋርጠው እንዲጓጓዙ ማስቻሉን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ በችግር ላይ ያለውን የሀገሪቱን የዱር እንስሳት ለመጠበቅ መንግስት ብዙ መስራት አለበት የሚሉት ሳይንቲስቶች ጥያቄ አንስተዋል፡፡
አቦሸማኔዎቹ አምስት ሴት እና ሶስት ወንዶች ሲሆኑ ከአፍሪካ ሳቫና ሁለት ቀን በአውሮፕላን እና በሄሊኮፕተር ከተጓዙ በኋላ በስድስት ስኩየር ኪ.ሜ ስፋት ባለው የፓርኩ ቦታ ከሁለት እስከ ሶስት ወራት እንዲቆዩ ተለቀዋል፡፡
ሁሉም አቦሸማኔዎች (ትላልቅ ድመቶች) የፓርኩ አየር ንብረት የሚስማማቸው ከሆነ አምስት ሺ ስኩየር ኪ.ሜ ስፋት ባለው የፖርኩ ክፍል እንዲንቀሳቀሱ ይደጋል፡፡
በቀጣይ ወር 12 የሚሆኑ አቦሸማኔዎቸ ከደበብ አፍሪካ ሲመጡ ቁጥሩን ከፍ ያርጉታል ተብሏል፡፡ንብረትነቱ የህንድ መንግስት የሆነው ኢንዲያን ኦይል አቦሸማኔዎች ለማብዛት ሚደረገውጥረት በገንዝብ ይደግፋል፡፡ ኢንዲያን ኦይል በህንድ የአቦሸማኔዎች ቁጥር 40 የማድረስ ተስፋ አለው፡፡