ህንድ በስህተት ወደ ፓኪስታን ሚሳዔል ያስወነጨፉ 3 የአየር ኃይል አመራሮችን አባረረች
ህንድ በድንገተኛው አጋጣሚ መጸጸቷን የገለፀች ሲሆን፤ ፓኪስታን ህንድን አስጠንቅቃለች
ህንድ ከወራት በፊት በስህተት ወደ ፓኪስታን ሚሳኤል አስወንጭፋለች
ህንድ ባሳለፍነው የካቲት ወር ላይ በስህተት ወደ ፓኪስታን ሚሳዔል ያስወነጨፉ ሶስት የአየር ኃይል አመራሮችን ማባረሯን አስታውቀለች።
ህንድ በስህተት ወደ ጎረቤቷ ፓኪስታን ሚሳኤል ማስወንጨፏን ተከትሎ ኒውክሌር በታጠቁ ሁለቱም ሀገራት መካከል ውጥረት እንዲሰፍን አድርጎ ቆይቷል።
ህንድ ሚሳኤሉን ያስወነጨፈችው የቴክኒክ ባለሙያዎች የጥገና ስራ ለመስራት በተንቀሳቀሱበት ጊዜ መሆኑን እና በድንገተኛ አጋጣሚው መጸጸቷን ገልጻ ነበር።
ፓኪስታን በበኩሏ ህንድ እንዲህ ዓይነቱ ቸልተኝነት የሚያስከትለውን መጥፎ ውጤት እንትገነዘብ እና እንዳይደገም ጥንቃቄ እንድታደርግ አስጠንቅቃለች።
የህንድ አየር ኃይል ባሳለፍነው ማክሰኞ እንዳሳወቀው፤ ከየካቲት 30 ክስተት ጋር በተያያዘ በወቅቱ በኃላፊነት ላይ የነበሩ ሰዎች ከቦታቸው እንዲነሱ መደረጉን አስታውቋል።
በተደረገው ምርመራም የስታንዳርድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም" መዛባት ብራህሞስ ሚሳኤል በአጋጣሚ መተኮሱን ማረጋገጡን አክሏል።
ህንድ በስህተት ወደ ፓኪስታን ያስወነጨፍው ሚሳዔል “ብራህሞስ” የሚባል ከሩዝ ሚሳዔል ሲሆን፤ ህንድ እና ሩሲያ በጋራ የሰሩት እና ኒውክሌር የመሸከም አቅም ያለው ነው።
የፓኪስታን አየር ኃይል እንዳስታወቁ ሚሳዔሉ ከድምጽ በሶስት እጥፍ በሚልቅ ፍጥነት ሲጓዝ እንደነበረ እና ከመሬት በ40 ሺህ ጫማ ከፍታ ላይ ሲበር ነበር።
ተመትቶ ከመውደቁ በፊትም የፓኪስታን አየር ክልልን ጥሶ በመግባት 124 ኪሎ ሜትር ገደማ መጓዙንም አስታውቋል።
የኑክሌር አረር ባለቤት የሆኑት ህንድ እና ፓኪስታን በካሽሚር ግዛት ይገባኛል በመወዛገብ ላይ ሲሆኑ በተደጋጋሚ ወደ ለየለት ጦርነት ይገባሉ የሚሉ ስጋቶች እንዳለ ነው።