በፈረንጆቹ ሰኔ 2020 በሁለቱ ሀገራት ወታደሮች መካከል በተፈጠረ ግጭት ቢያንስ 20 የህንድ እና አራት የቻይና ወታደሮች መሞታቸው ይታወሳል
የሕንድ እና የቻይና ወታደሮች በነገው እለት አወዛጋቢ ከሆነው የሩቅ ምዕራባዊ ሂማሊያን ድንበር አካባቢ እንደሚለቁ የሕንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አርብ ዕለት አስታውቋል፡፡
ይህ ወሳኔ የተላለፈው በድንበሩ አካባቢ ተከስቶ የነበረውን ደም አፋሳሽ ግጫት ተከትሎ ከመጣው የሁለት አመታት ፍጥጫ በኋላ ነው፡፡
በከፍተኛ ወታደራዊ ባለስልጣናት መካከል ከበርካታ ዙር ንግግሮች በኋላ የመጣው ይህ ስምምነት በ1962 በድንበራቸው ላይ ጦርነት በፈጠሩት ኒውክሌር የታጠቁ የኤዥያ ግዙፍ ሃይሎች መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ለማስቀረት ኒው ዴሊ እና ቤጂንግ ያደረጉት ጥረት አካል ነው።
የወታደሮቹ መውጣት በቻይና በኩልም ተረጋግጧል ተብሏል፡፡ የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በሚቀጥለው ሳምንት ኡዝቤክስታን በሚደረገው ስብሰባ ላይ እንደሚገናኙ ይጠበቃል፡፡
የህንድ እና የቻይና ወታደሮች ሃሙስ እለት በምእራብ ሂማላያ በላዳክ ከሚገኘው የጎግራ-ሆት ስፕሪንግስ አካባቢ መውጣት ጀምረዋል ብሏል የህንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አሪንዳም ባግቺ በሰጡት መግለጫ "ሁለቱ ወገኖች በዚህ አካባቢ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን በደረጃ፣ በተቀናጀ እና በተረጋገጠ መንገድ ለማቆም ተስማምተዋል፤ በዚህም ምክንያት የሁለቱም ወገኖች ወታደሮች ወደየአካባቢያቸው እንዲመለሱ ተደርጓል" ብለዋል።
በሁለቱም ወታደሮች በተገነባው አካባቢ ያሉ ሁሉም ጊዜያዊ መዋቅሮችም በስምምነቱ መሰረት ይፈርሳሉ ብለዋል።
በቅርቡ የተደረሰው ስምምነት ዝርዝር ይፋ ባይሆንም የሁለቱ ሀገራት ወታደሮች በወታደሮቻቸው መካከል መከላከያ ፈጥረው በአካባቢው የሚያደርጉትን ቅኝት ሊያቆሙ እንደሚችሉ የመከላከያ ኤክስፐርት ተናግረዋል።
በላዳክ ያገለገሉት የህንድ ሌተና ጄኔራል ራኬሽ ሻርማ "ይህ አዎንታዊ እርምጃ ነው" ብለዋል። "የፊት ለፊት ሁኔታ ተወግዷል።"
በፈረንጆቹ ሰኔ 2020 ቢያንስ 20 የህንድ እና አራት የቻይና ወታደሮች የሞቱበትን ግጭት ተከትሎ፣ ወታደሮች በቅርብ በተሰማሩባቸው በላዳክ ውስጥ ሌሎች አካባቢዎች ተመሳሳይ የመከላከያ ቦታዎችን ይአዋል፡፡
ነገር ግን ሻርማ እንዳሉት የሁለቱም ወገኖች ወታደሮች በላዳክ ውስጥ በዴምቾክ አካባቢ አቅራቢያ ቢያንስ አንድ ቦታ በቅርብ ርቀት ላይ እንደሚቆዩ እና ይህም በቀጣይ ንግግሮች ሊወሰድ ይችላል ብለዋል፡
ህንድ እና ቻይና 3800 ኪ.ሜ ያልተካለለ ድንበር ይጋራሉ፡፡