የዓለማችን ቀዳሚ የአልኮል መጠጥ ተጠቃሚ ሀገራት እነማን ናቸው?
የዓለም ጤና ድርጅት ዓመታዊ የአልኮል መጠጥ ሪፖርትን ይፋ አድርጓል
እንደ ሪፖርቱ ከሆነ የአልኮል መጠጥ ፍጆታ በ21 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል ተብሏል
የዓለማችን ቀዳሚ የአልኮል መጠጥ ተጠቃሚ ሀገራት እነማን ናቸው?
የዓለም ጤና ድርጅት ዓመታዊ የአልኮል ፍጆታ ሪፖርትን ይፋ ያደረገ ሲሆን በሪፖርቱ መሰረት አውሮፓ ቀዳሚ የጠጪዎች አህጉራ ተብላለች።
በአውሮፓ አንድ ዜጋ በአማካኝ በዓመት ንጹህ 10 ሊትር አልኮል ወይም 190 ሊትር ቢራ እንደሚጠጣ ተገልጿል።
ይህ የአልኮል ፍጆታ ሪፖርት ከ2020 ጋር ሲነጻጸር በ21 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል የተባለ ሲሆን የገቢ መቀነስ እና ኮሮና ቫይረስ ዋነኛ ምክንያት ናቸውም ተብሏል።
በዚህ ሪፖርት መሰረትም በዓለማችን ካሉ አስር ቀዳሚ የአልኮል ሸማች ሀገራት ውስጥ ዘጠኙ የአውሮፓ ሀገራት እንደሆኑ ተገልጿል።
ወንዶች ከሴቶች የበለጠ መጠን ያለው አልኮል ይወስዳሉም ተብሏል።
ቸክ ሪፐብሊክ፣ ላቲቪያ፣ ሞልዶቫ፣ ጀርመን፣ ሊቱኒያ፣ አየርላንድ፣ ስፔን፣ ቡልጋሪያ እና ሮማኒያ ከፍተኛ የአልኮል ፍጆታ ያለባቸው ሀገራት ዝርዝር ውስጥ ተካተዋል ሲል ዩሮ ኒውስ ዘግቧል።
ከአፍሪካ ደግሞ ኡጋንዳ፣ ታንዛኒያ እና ቡርኪናፋሶ በአንጻራዊነት ከፍተኛ የአልኮል ተጠቃሚዎች እንዳሉ ይሄው ሪፖርት ጠቅሷል።
እንደ ዓለም ጤና ድርጅት የ2019 ሪፖርት መሰረት በኢትዮጵያ አንድ ሰው በአማካኝ 2 ነጥብ 2 ሊትር አልኮል ይጠቀማል።
ሳውዲ አረቢያ፣ ሶማሊያ፣ ባንግላዲሽ፣ ኩዌት እና ሞሪታንያ ምንም አይነት የአልኮል መጠጥ ተጠቃሚ ዜጎች እንደሌላቸው በሪፖርቱ ላይ ተጠቅሷል።