የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንደገለጸው ቻይና ይህን እርምጃ የወሰደችው የቻይናን ከፍተኛ ጥራት ያለውን እድገት ለማስተዋወቅ ነው
ቻይና ለስድስት ሀገራት ከቪዛ ነጻ ጉዞ መፍቀዷን አስታወቀች።
ቻይና ለአንድ አመት ያለቪዛ ወደ ሀገሯ እንዲገቡ የፈቀደችው ለፈረንሳይ፣ ለጀርመን፣ ለጣሊያን፣ ለኔዘርላንድስ፣ ለስፔን እና ለማሌዥያ ዜጎች መሆኑን የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
በፈረንጆቹ ከመስከረም 30፣2024 ጀምሮ ፖሰፖርት ያላቸው የእነዚህ ሀገራት ተራ ዜጎች ለጉብኝት ወይም ለስራ ወደ ቻይና ተጉዘው ለ15 ቀናት ያህል መቆየትየ ይችላሉ ተብሏል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ማኦ ኒንግ እንደገለጹት ቻይና ይህን እርምጃ የወሰደችው የቻይናን ከፍተኛ ጥራት ያለውን እድገት ለማስተዋወቅ ነው።
በአሁኑ ወቅት በርካታ ተጓዦች ቻይናን ለማየት ቪዛ ይፈልጋሉ
ወደ ቻይና ለስራ፣ለቤተሰብ ጥየቃ እና ለጉብኝት ቻይና ሲገቡ የነበሩት የሲንጋፖር እና የብሩናይ ዜጎች ያለቪዛ የመግባት መብት ሳይፈቀድላቸው ቀርቷል።
ቻይና ወደ ሀገሯ በሚገቡ ዜጎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ማድረግ የጀመረችው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽን ከተከሰተ በኋላ ነበር።
ቻይና ላለፉት ሶስት አመታት በርካታ ምርመራዎችን በማድረግ፣ መንገድ በመዝጋት እና ጥብቅ የጉዞ እገዳ በማድረግ ኮሮናን ለመከላከል ከአለም ጥብቅ የሚባሉ እርምጃዎችን መውሰዷ ይታወሳል።
ኮሮና ከመከሰቱ ቀደም ብሎ በ10 ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ቻይን ይጎበኙ ነበር።