ቻይና ለዓለም በሬን ለመክፈት ቁርጠኛ ነኝ አለች
በ78ተኛው የመንግስታቱ ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ቤጂንግ ሉዓላዊነቷንና የግዛት አንድነቷን ለመጠበቅ ያላትን ቁርጠኛነት ገልጻለች
ቤጂንግ ልዩነቶችና አለመግባባቶች በሰላማዊ መንገድ መፈታት አለባቸው ብላለች
የቻይና ምክትል ፕሬዝዳንት ሀን ዜንግ ቤጂንግ ለተቀረው ዓለም በሯን ለመክፈት ቁርጠኛ መሆኗን ተናግረዋል።
ሀገሪቱ በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት ትልቅ ቤተሰብ ሁሌም አባል መሆኗንም ትቀጥላለች ብለዋል።
ምክትል ፕሬዝዳንቱ በ78ተኛው የመንግስታቱ ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ቻይና ነጻ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲና ሉዓላዊነቷንና የግዛት አንድነቷን ለመጠበቅ ያላትን ቁርጠኛነትም ገልጸዋል።
"የሁሉም ሀገራት ተገቢ የደህንነት ስጋቶች ሊፈቱ ይገባል።የእያንዳንዱ ሀገራት ሉዓላዊነቷንና የግዛት አንድነት ሊከበር ይገባል። ልዩነቶችና አለመግባባቶች በሰላማዊ መንገድ በውይይትና በምክክር መፈታት አለባቸው" ብለዋል።
የዩክሬን-ሩሲያ ጦርነትን በተመለከተ ሀገራቸው ለሰላም የሚደረጉ ጥረቶችን እንደምትደግፍ የተናገሩት ሀን ዜን፤ ቻይና ወደ ሰላም ለሚወስዱ መንገዶች ገንቢ ሚና ለመጫወት ዝግጁነቷን ትቀጥላለች ሲሉ ተናግረዋል።
የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዋንግ ይ ለሩሲያው አቻቸው ሰርጌ ላቭርቭ ቤጂንግ በዩክሬን ጉዳይ ነጻነትን የሚያከብር አድልኦ የለሌበት አቋም ትይዛለች ማለታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ቤጂንግ ጸብአጫሪ የተባለችውን ሩሲያን ለማውገዝ አሻፈረኝ በማለቷ ከምዕራባዊያን ትችት ተሰንዝሮባታል።