ቤጂንግ አንድ በርሜል የኢራንን እና ቬንዙዌላን ነዳጅ ከ10-15 ዶላር መግዛቷ ተገልጿል
ቻይና የሩሲያን ጋዝ በመግዛቷ 10 ቢሊዮን ዶላር ማትረፏ ተገለጸ፡፡
ሩሲያ ጦሯን ወደ ዩክሬን መላኳን ተከትሎ በአሜሪካ፣ አውሮፓ ህብረት እና ሌሎች ሀገራት ከ12 ሺህ በላይ ማዕቀቦች ተጥለውባታል፡፡
በማዕቀቡ ምክንያትም ዋነኛ የነዳጅ ግብይት ስትፈጽምባቸው የነበሩ የአውሮፓ ሀገራትም ፊታቸውን ወደ ሌላ ሀገራት ሊያዞሩ ችለዋል፡፡
ሌላኛዎቹ ኢራን እና ቬንዙዌላም በምዕራባዊያን ሀገራት ማዕቀብ የተጣለባቸው ሀገራት ሲሆኑ ሀገራቱ በዋናነት ነዳጃቸውን ለዓለም ገበያ ማቅረብ አልቻሉም፡፡
እነዚህ የምዕራባዊያን ማዕቀቦች ለዓለማችን ሁለተኛዋ ልዕለ ሀያል ሀገር ቻይና ጥሩ የገበያ እድል እንደፈጠረላት ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
እንደ ዘገባው ከሆነ በነዳጅ ሀብታቸው የበለጸጉት ሩሲያ፣ ኢራን እና ቬንዙዌላ በምዕራባዊያን ሀገራት ማዕቀብ መጣሉ ነዳጃቸውን ለቻይና ረከስ ባለ ዋጋ እንዲሸጡ አድርጓል ተብሏል፡፡
አሜሪካ የሩሲያን መከላከያ ይደግፋሉ ባለቻቸው 42 የቻይና ኩባንያዎች ላይ የንግድ ገደብ ጣለች
በተያዘው የፈረንጆቹ 2023 ዓመት ባሉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ ቻይና ከሶስቱ ሀገራት 2 ነጥብ 7 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ እንደገዛች ተገልጿል፡፡
ቻይና ማዕቀብ ለተጣለባቸው ሶስቱ ሀገራት ጥሩ የገበያ አማራጭ ሆናለች የተባለ ሲሆን በአንጻሩ ቻይናም ያለፉክክር የሀገራቱን ነዳጅ እንድትገዛ አስችሏታልም ተብሏል፡፡
ቻይና የሩሲያን ነዳጅ በመግዛቷ ብቻ ከ4 ቢሊዮን ዶላር በላይ አትርፋለች የተባለ ሲሆን አንድ በርሜል የቬንዙዌላን ነዳጅ በ10 ዶላር እንዲሁም አንድ በርሜል የኢራንን ነዳጅ ደግሞ በ15 ዶላር እንደገዛች ተገልጿል፡፡