ፊሊፒንስ ከደቡባዊ ቻይና ባህር ጋር በተያያዘ የቤጂንግ ዲፕሎማቶች እንዲባረሩ ወስናለች
ቻይና የአሜሪካ ጦር መርከብን ማባረሯን ገለጸች፡፡
ቻይና የእኔ ነው የምትለው ደቡባዊዊ ቻይና ባህር አምስት ሀገራት የእኔ ነው በሚል ይወዛገቡበታል፡፡
ይህ ባህር የእኔ ነው ከሚሉ ሀገራት መካከል ፊሊፒንስ፣ ቬትናም፣ኢንዶኔዢያ፣ ማሌዢያ እና ብሩኔ ይወዛገቡበታል፡፡
ይ ባህር የእኔ ነው ከሚሉ ሀገራ መካከል ከቻይና ውጪ ካሉት ሀገራት ጋር መልካም ግንኙነት ያላት አሜሪካ ደግሞ በዚህ ባህር አካባቢ የጦር መርከቧን ታሰማራለች፡፡
የቻይና ጦርም ይህን ሀስሌይ የተሰኘ ስያሜ ያለው የአሜሪካ ግዙፍ የጦር መርከብ በሀይል ማባረሩን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
እንደዘገባው ከሆነ የቻይና ህዝባዊ ጦር የአሜሪጦር መርከብ እንቅስቃሴ የቻይናን ሉዓላዊነትን የሚጥስ ነው ያለ ሲሆን በአካባቢው ቅኝት እያደረገ እና ጥብቅ ጥበቃ በማድረግ ላይ መሆኑን አስታውቋል፡፡
አሜሪካ የጦር መርከቧን ወደ ታይዋን ሰርጥ መላኳ ቻይናን አስቆጣ
ፊሊፒንስ በበኩሏ ከዚሁ ደቡባዊ ቻይና ባህር ጋር በተያያዘ በማኒላ ያሉ የቻይና ዲፕሎማቶችን እንደምታባርር አስታውቃለች፡፡
ቻይና የፊሊፒንስ ባህር ሀይል አዛዥ የስልክ ልውውጥን በመጥለፍ የተሳሳተ መረጃ አሰራጭታለች ስትልም ከሳለች፡፡
ቻይና በበኩሏ የፊሊፒንስ ድርጊት ጸብ አጫሪነት በመሆኑ ከዚህ ድርጊቷ እንድትታቀብ አስጠንቅቃለች፡፡
የጦር መርከቧን ወደ አዋዛጋቢው ቦታ የላከችው አሜሪካ በደቡባዊ ባህር ሀይል ዙሪያ ስለተፈጠሩ ድርጊቶች ዙሪያ እስካሁን ምላሽ ከመስጠት ተቆጥባለች፡፡