ቻይና፤ ዶ/ር ቴድሮስ ኃላፊነት የጎደለው መግለጫ ከመስጠት እንዲቆጠቡ አሳሰበች
ኮሮና ቫይረሳ መጀመሪያ ሪፖረት የተደረገው በፈረንጆቹ 2019 በቻይናዋ ሁቤ ግዛት ነበር
ቻይና ይህን ያለችው ዶ/ር ቴድሮስ የቻይናን “የዜሮ ኮሮና” ፖሊስ ዘለቄታ የለውም ማለታቸውን ተከትሎ ነው
የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ኃላፊነት የጎደለው መግለጫ ከመስጠት እንዲቆጠቡ አሳስበዋል፡፡
ቻይና ይህን ያለችው ዶ/ር ቴድሮስ የቻይና የዜሮ ኮሮና ፖሊስ ዘለቄታ የለውም ማለታቸውን ተከትሎ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዛዎ ልጃን በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ የቻይና እርምጃ ትክክል ነው፤ የአለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተርም የቻይናን የኮሮና ፖሊሲ በፍትሃዊነት እንደሚያዩት ተስፋ አለኝ ብለዋል፡፡
ዶ/ር ቴድሮስ እስካሁን የቫይረሱ ባለው መረጃ መሰረት የቻይና የኮሮና ዜሮ ፖሊስ ዘለቄታ የለውም በማለት አስተያየት ሰጥተው ነበር፡፡
የቫይረሱ ባህሪይ ስናየው እና ወደፊት ያለውም ስንገምት የቻይና ፖሊስ ዘለቄታ ያለው ነው ብለዋል እንዳማያስቡ ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡ በዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም አስተያያት ቻይና አልተቀበለችም፡፡
በታህሳስ 2019 በቻይና ሁቤ ግዛት የተቀሰቀሰው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መላውን አለም በማዳረስ በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ሰዎች እንዲሞቱ እና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ደግሞ እንዲጠቁ ምክንያት ሆኗል፡፡
ቫይረሱ በኢትዮጵያ መጋቢት ወር በ2012ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ መግባቱ ይፋ መሆኑ ይታወሳል፡፡