ዶ/ር ቴድሮስ ከህወሓት ጋር ወግነዋል የሚለው ክስ “አውነት አይደለም” አሉ
“እኔ በአንድ ወገን ብቻ ነኝ፤ይሄውም በሰላም ወገን ነው” ብለዋል ዶክተር ቴድሮስ
ዶክተር ቴድሮስ በተፈጠረው ሁኔታ “ልቤ ተሰብሯል” ሁሉም አካላት ለሰላም እንዲሰሩና የሰላማዊ ዜጎችን ደህንነት እንዲጠብቁ ጥሪ አቅርበዋል
ዶክተር ቴድሮስ በተፈጠረው ሁኔታ “ልቤ ተሰብሯል” ሁሉም አካላት ለሰላም እንዲሰሩና የሰላማዊ ዜጎችን ደህንነት እንዲጠብቁ ጥሪ አቅርበዋል
የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተርና የቀድሞው የህወሓት አባል የሆኑት ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በትዊተር ገጻቸው ኢትዮጵያ ውስጥ በተፈጠረው የፌደራል መንግስትና የህወሓት ግጭት ከህወሓት ጋር ወግነዋል የሚለው ክስ እውነትነት የለውም ብለዋል፡፡
“በሁኔታው ላይ ለአንዱ እንደወገንኩ የሚያሳዩ ሪፖርቶች አሉ፡፡ይሄ እውነት አይደለም፤እኔ በአንድ ወገን ብቻ ነኝ፤ይሄውም በሰላም ወገን ነው” ብለዋል ዶክተር ቴድሮስ፡፡
ዶክተር ቴድሮስ ይህን ያሉት የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄነራል ብርሀኑ ጁላ ዶ/ር ቴድሮስ “የዓለም አቀፍ ተልዕኮ ዕድሉን ተጠቅሞ የህወሓትን ጁንታ ለመርዳት ያላደረገው ጥረት የለም” የሚል ክስ መሰንዘራቸውን ተከትሎ ነው፡፡
ጄነራል ብርሃኑ “ሰውየ[ዶ/ር ቴድሮስ] ራሱ የዛ ቡድን አባል፤ እንደምታውቁትም ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ነው” ስለሆነም ለህወሓት መወገኑ የሚጠበቅ ነው ብለው ነበር፡፡
ዶክተር ቴድሮስ የጄነራል ብርሃኑና ሌሎች ክሶችን እውነት አለመሆናቸውም ገልጸዋል፡፡
ዶክተር ቴድሮስ ኢትዮጵያ ውስጥ በተፈጠረው ሁኔታ “ልቤ ተሰብሯል” ሁሉም አካላት ለሰላም እንዲሰሩና የሰላማዊ ዜጎችን ደህንነት እንዲጠብቁ፣የጤና አገልግሎት እንዲያገኙና የሰብአዊ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው እርዳታ እንዲያገኙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በግጭቱ ምክንያት የደረሰው ጉዳትና ሰዎች ተፈናቅለው ወደ ጎረቤት ሀገራት እየገቡ መሆናቸው እንዳሳዘናቸው ዶክተር ቴድሮስ ገልጸዋል፡፡
ዶክተር ቴድሮስ “ግጭቱ በፍጥነት እንዲረግብና ለግጭቱ ሰላማዊ መፍትሄ ይፈለግ” የሚለውን የተባበሩት መንግስታትን(ተመድ) ጥሪ የሚጋሩ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡
አለምአቀፍ የበሽታ ወረርሽኝ ባለበት ወቅት ሁኔታው በጤና ላይ የሚያደርሰው አሉታዊ ተጽእኖ እንደሚያሳስባቸው
በፌደራል መንግስትና በህወሓት መካከል የነበረው አለመግባባት ወደ ግጭት ያመራው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጥቅምት 24 ህወሓት በትግራይ ክልል ባለው የሰሜን እዝ የመከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት አድርሷል፤እርምጃም እንደሚወሰድ ማሳወቃቸውን ተከትሎ ነው፡፡ግጭቱ ከተጀመረ ከሁለት ሳምንት በላይ ሆኖታል፡፡