
ቡድኑ ቻይናን በበርካታ ሀገራት ጉዳዮች ዙሪያ የወቀሰ መግለጫ አውጥቷል
ቻይና የቡድን ሰባት ሀገራትን “ትዕቢተኞች” ስትል ጠራች፡፡
በዓለማችን ሰባት ቀዳሚ ኢኮኖሚ ያላቸው ሀገራት ወይም በተለምዶ ቡድን ሰባት ተብሎ የሚጠራው ቡድን በካናዳዋ ኩቤክ ያደረገውን ጉባኤ አጠናቋል፡፡
በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የተወከለው ይህ ጉባኤ ቻይና በእስያ እና አውሮፓ እያደረገች ያለውን እንቅስቃሴ ኮንኖ መግለጫ አውጥቷል፡፡
እንደ መግለጫው ከሆነ ቻይና በታይዋን፣ ደቡባዊ ቻይና ባህር፣ በአውስትራሊያ እና በምስራቅ አውሮፓ ሀገራት ላይ እያደረገች ያለው እንቅስቃሴ የደህንነት ስጋት ደቅኗል ብሏል፡፡
ቻይና ካናዳ በሚገኘው ኢምባሲዋ በኩል ለቡድን ሰባት መግለጫ ምላሽ የሰጠች ሲሆን ቡድኑ በትዕቢት የተሞላ ነው ብላለች፡፡
ደቡባዊ ቻይና እና ታይዋን የግዛቷ አንድ አካል ሆነው እያለ በቻይና የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ገብቶ መግለጫ መውጣቱንም ቤጂንግ ኮንናለች፡፡
ቻይና አስፈላጊ ከሆነ በታያዋንን ለመጠቅለል ሀይል ልትጠቀም እንደምትችል የገለጸች ሲሆን የቡድን ሰባት በሉዓላዊ ሀገር የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ እንዳይገባም አስጠንቅቃለች፡፡
እንደ ቡድን ሰባት መግለጫ ከሆነ ቻይና በታይዋን የአየር ክልል ውስጥ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ማድረግ፣ በደቡባዊ ቻይና ባህር የፊሊፒንስን ሉዓላዊነት የሚጥስ እንቅስቃሴ አድርጋለች፡፡
እንዲሁም ታስማን ተብሎ በሚጠራው በስዋዚላንድ እና አውስትራሊያ አዋሳኝ የባህር መስመር ላይ ያለ ሁለቱ ሀገራት እውቅና ወታደራዊ ልምምድ እንዳደረገችም ተገልጿል፡፡
የቻይና እንቅስቃሴ የሀገራትን ሉዓላዊነት የሚጥስ ነው ያለው የቡድን ሰባት ሀገራት መግለጫ ከቤጂንግ ጠንካራ ምላሽ እንደተሰጠው ኤፒ ዘግቧል፡፡
ባላት የባህር ሀይል ጥንካሬ የዓለማችን ቁጥር አንድ ሀገር የሆነችው ቻይና በእስያ እና አፍሪካ የባህር ሀይል ማዘዣዎችን ገንብታለች፡፡