ቻይና የልጆችን የስልክ አጠቃቀም በቀን ለሁለት ሰዓት ልትገድብ ነው
አገልግሎት አቅራቢዎች ኢንተርኔት እንዳይጠቀሙ የሚከለክሉ መጠነኛ መርሃ-ግብሮችን እንዲያስተዋውቁ ተናግሯል
በእርምጃው ቻይና የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የአክሲዮኖች ድርሻ መቀነሱ ተሰምቷል
የቻይናው የሳይበር ስፔስ ተቆጣጣሪ ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት በስማርት ስልኮቻቸው ላይ በቀን ቢበዛ ለሁለት ሰዓት እንዲገደቡ ሊያደርግ ነው።
የቻይና የሳይበር ስፔስ አስተዳደር የስማርት መሳሪያዎች አቅራቢዎች እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ተጠቃሚዎች ከ10 ሰዓት እስከ 6 ሰዓት በተንቀሳቃሽ መሳሪያዎች ላይ ኢንተርኔት እንዳይጠቀሙ የሚከለክሉ መጠነኛ መርሃ-ግብሮችን እንዲያስተዋውቁ እንደሚፈልግ ተናግሯል።
አገልግሎት አቅራቢዎች በታቀደው ማሻሻያ መሰረት የጊዜ ገደቦችን ማውጣት አለባቸው ሲል ተናግሯል።
እድሜያቸው ከ16 እስከ 18 የሆኑ ተጠቃሚዎች በቀን ሁለት ሰዓት፤ ከ8 እስከ 16 ዓመት የሆኑ ህጻናት አንድ ሰዓት ብቻ እንዲጠቀሙ ይፈቀዳል ተብሏል።
ከስምንት ዓመት በታች ለሆኑ ህጻናት ደግሞ ስምንት ደቂቃ ብቻ ይፈቀድላቸዋል።
ነገር ግን ተቆጣጣሪው አገልግሎት አቅራቢዎች ወላጆች ለልጆቻቸው የተወሰነ የጊዜ ገደብ እንዲያወጡ መፍቀድ አለባቸው ብሏል።
ሆኖም ባለሀብቶች በእርምጃው አለመደነቃቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
የሳይበር ስፔስ አስተዳደር ረቂቅ መመሪያዎቹን ካወጣ በኋላ የቻይና የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የአክሲዮን ድርሻ መቀነሱ ተነግሯል።