ቻይና ጦሯ አዳዲስ የኒውክሌር ጦር መሳሪያዎችን መታጠቁን አስታወቀች
ቻይና የኒውክሌር ጦር መሳሪያዎችን በማዘጋጀት ረገድ ትልቅ ደረጃ ላይ መድረሷን ገለፀች
የቻይና መከላከያ ሚ/ር “ከሌሎች ጋር የጦር መሳሪያ ሽቅድምድም ውስጥ መግባት አንፈልግም” ብለዋል
ቻይና በታጠቀችው አዳዲስ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ዙሪያ አስተያየት ሰጥታለች።
የቻይና መከላከያ ሚኒስትር ዌይ ፌንጌ ዛሬ እሁድ በሰጡት አስተያየት፤ “ቻይና አዳዲስ የኒውክሌር ጦር መሳሪያዎችን በማዘጋጀት ረገድ ትልቅ እድገት አሳይታለች” ብለዋል።
ሆኖም ግን የኒውክሌር ጦር መሳሪያዎቹን በቅርቡ ጥቅም ላይ የማዋል ፍላጎት እንደሌላትም ሚኒስትሩመናተራቸውን የሩሲያው አር ቲ ዘግቧል።
አዳዲሶቹ የጦር መሳሪያዎች በአሁኑ ወቅት የቻይና ጦር እንዲታተቃቸው ተደርጓል ያሉት ሚኒስትሩ ሆኖም ግን “ከሌሎች ጋር የጦር መሳሪያ ሽቅድምድም ውስጥ መግባት አንፈልግም” ብለዋል።
ቻይናም ራስን የመከላከል የኒውክሌር ፖሊሲዋን መከተሏን እንደምትቀጥልም የመከላከያ ሚኒስትሩ ዌይ ፌንጌ ተናግረዋል።
የቻይና የኒውክሌር ፖሊሲ “የኒውክሌር የጦር መሳሪያዎች “ብሔራዊ ሰላምን ለመጠበቅ እና የኑክሌር ጦርነትን ጥፋት ለማስወገድ” እንደሚውል ያትታል።
ቻይና ቀርብ ጊዜ ወዲህ በታይዋን ጉዳይ ከአሜሪካ ጋር እሰጣ ገባ ውስጥ መግባታቷን ተከትሎ የተለያዩ ወታደራዊ ልምምዶችን እያካሄደች መሆኑ ያታወቃል።
በቅርቡም ለአሜሪካ ማስጠንቀቂያ ያለችውን ወታደራዊ ልምምድ የባህር ኃይሏን እና የአየር ኃይሏን በማሳተፍ በታይዋን ዙሪያ ማድረጓ ይታወቃል።
የቻይና የመከላከያ ሚኒስትር ዌዪ ፈንጊሄ ከአሜሪካው የመከላከያ ሚኒስትር ሎልዩድ አውስቲን ጋር ባደረጉት ቆይታም ቻይና በታይዋን ጉዳይ እንደማትደራደርና ውጊያ መግጠም ካለባትም ለመግጠም ዝግጁ መሆኗን ተናግረዋል።