ሩሲያ እና ቻይና ምዕራባውያንን የሚያስኮርፍ ስምምነት ተፈራረሙ
ፕሬዝደንት ዢ ከሁለት ወራት በፊት ወደ ሩሲያ በማቅናት ከፑቲን ጋር ውይይት ማድረጋቸው ይታወሳል
ሁለቱ ሀገራት ትብብራቸውን እያጠናከሩ ሲሆን ምዕራባውያን ሀገራት ከዩክሬን ጦርነት በኋላ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነትን በጥንቃቄ እየተመለከቱት ነው
የሩሲያ ጠቅላይ ሚኒስቴር በዛሬው እለት ወደ ቻይና የሚሄዱ ሲሆን በዚሁ ወቅት ሩሲያ እና ቻይና የተለያዩ ስምምነቶችን ተፈራርመዋል።
ሁለቱ ሀገራት ትብብራቸውን እያጠናከሩ ሲሆን ምዕራባውያን ሀገራት ከዩክሬን ጦርነት በኋላ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነትን በጥንቃቄ እየተመለከቱት ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ሚካሂል ሙሽቲን ሩሲያ በዩክሬን ላይ ልዩ ያለችውን ወታደራዊ ዘመቻ ከከፈተች በኋላ ቻይናን የጎበኙ ከፍተኛ የሩሲያ ባለስልጣን ይሆናሉ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከቻይናው ፕሬዝደንት ዢ ጅንፒንግ ጋር ይገናኛሉ ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።
የሩሲያ ኢንተርፋክስ ዜና አገልግሎት እንደዘገበው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፕሬዝደንት ዢ ጅንፒንግ ጋር ከተወያዩ በኋላ በርካታ የሁለትዮሽ ስምምነቶች ይፈረማሉ።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት ሩሲያ እና ቻይና የቡድን ሰባት ሀገራት በዩክሬን፣ በኑክሌር ጦር መሳሪያ እና በኢኮኖሚ ፖሊሲ ጉዳዮች ጨምሮ በበርካታ ጉዳዮች በመገለላቸው ያሳዩትን ቁጣ ተከትሎ የመጣ ነው ተብሏል።
ፕሬዝደንት ዢ ከሁለት ወራት በፊት ወደ ሩሲያ በማቅናት ከፑቲን ጋር ውይይት ማድረጋቸው ይታወሳል።
ሩሲያ በዩክሬን ላይ ልዩ ያለችውን ወታደራዊ ዘመቻ ከመክፈቷ በፊት በፈረንጆቹ 2022 ሁለቱ ሀገራት "ገደብ የሌለው" ወዳጅነት ለመመስረት ተስማምተው ነበር።
ምዕራባውያን ቻይና ከሩሲያ ጋር ያላትን ግንኙነት ከዩክሬን ጦርነት ጋር በማያያዝ ተገቢ አለመሆኑን ቢገልጹም ቻይና ግን ህግ አለመጣሷን እና ከማን ጋር በመተባበር እንዳለባት የመምረጥ መብት አላት ስትል ገልጻለች።