ህንድና ቻይና የድንበሩን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ተስማሙ
በፈረንጆቹ በ1962 በሁለቱ ሀገራት መካከል የተካሄደውን ደምአፋሳሽ ጦርነት እንዳይቀሰቅሰው ተሰግቷል
ህንድና ቻይና በመካከላቸው ያለውን የድንበር ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት መስማማታቸውን የህንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ
ህንድና ቻይና በመካከላቸው ያለውን የድንበር ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት መስማማታቸውን የህንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ
ህንድና ቻይና በላዳክህ ግዛት በሚጋሩት ድንበር ምክንያት ያላቸውን አለመግባባት ዲፕሎማሲያዊ በሆነ መንገድ ለመፍታት መስማማታቸውን የህንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ይህን መግለጫ ያወጣው የሁለቱ ሀገራት ከፍተኛ ጄነራሎች ግጭቱ በተፈጠረበት አካባቢ ተገኝተው ውጥረቱን ለማርገብ ከሚያደርጉት ስብሰባ አንድ ቀን ቀደም ብሎ ነው፡፡
የህንድ ባለስልጣናት ሁለቱም አካለት ማተኮር ያለባቸው ግጭት ወደተፈጠረበት ቦታ የተላኩትን የህንድን ጦርና የቻይናን ላይብሬሽን ጦር ወደ ኋላ እንዲያፈገፍጉ ማድረግ ነው ብለዋል፡፡
ከሁለቱም ወገን ወታደሮች በከፍተኛ ቦታ በምትገኘው በላዳክ ግዛት ውስጥ በሚገኘው ጋልዋን በሚባል ሸለቆ ሰፍረው ድንበር መበጣስ እርስበእርስ እየተካሱ ይገኛሉ፡፡ይህም በፈረንጆቹ በ1962 በሁለቱ ሀገራት መካከል ለአጭር ጊዜ የተካሄደውን ደምአፋሳሽ ጦርነት እንዳይቀሰቅሰው ተሰግቷል፡፡
እንደ ህንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሆነ የሁለቱ ሀገራት የባለስልጣናት በቪዲዮ ኮንፈረንስ በመካከላቸው ያለውን ልዩነት በሰላማዊ ውይይት መፍታት እንዳለባቸው ተወያይተዋል፡፡
በቤጂንግ በኩል የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃልአቀባይ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በቻይናና ህንድ ድንበር ያለው ጠቅላላ ሁኔታ የተረጋጋና መቆጣጠር የሚቻል መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ቅርብ በሆነ ወታደራዊና በዲሎማሲያው ንግግር ሁለቱም ወገኖች አስፈላጊ ነገሮችን በሰላም ለመፍታት እየሰሩ መሆኑን ቃል አቀባዩ ተራግሯል፡፡
ሁለቱም ሀገራት ሰላማዊ፣ የተረጋጋና ሚዛናዊ የሆነ ግንኙት ለመፍጠር ስምምነት ላይ መድረስ አስፈላጊ መሆኑን ስምምነት መደረሱን የህንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያወጣው መግለጫ ያመለክታል፡፡