ሩሲያ ከአንድ ዓመት በፊት 147 ሺህ ወታደሮችን መመልመሏ ይታወሳል
ሩሲያ ተጨማሪ 150 ሺህ ወታደሮችን ልትመለምል መሆኗን አስታወቀች፡፡
በዩክሬን ምድር ከኔቶ ጋር እየተዋጋች መሆኗን የገለጸችው ሩሲያ ተጨማሪ 150 ሺህ ወታደሮችን ልትመለምል መሆኗን አስታውቃለች፡፡
ፕሬዝዳንት ፑቲንም ሩሲያ አዲስ 150 ሺህ ወታደሮችን መመልመል የሚያስችለውን ህግ በፊርማቸው አንዳጸደቁ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ዘገባው አክሎም ሩሲያ የጸደይ ወራት በሚባሉት ሚያዝያ እና ግንቦት ወራት ውስጥ ምልመላውን ለማጠናቀቅ እቅድ ስለመያዙ ተገልጿል፡፡
የሩሲያ ምክር ቤት የሀገሪቱን ጦር ለመቀላቀል አስቀምጦት የነበረውን የእድሜ ጣራ ከ27 ዓመት ወደ 30 ዓመት ከፍ እንዲል ወስኗል፡፡
ሩሲያ ለሁሉም የዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ወታደራዊ ስልጠናዎችን እንዲወስዱ የምታስገድድ ሲሆን በየዓመቱ በ100 ሺህዎች የሚቆጠሩ ሩሲያዊያን ስልጠና እየወሰዱ ይመረቃሉ፡፡
ሩሲያ ከሞስኮው ጥቃት ጀርባ አሉ ያለቻቸውን ሶስት ሀገራት ይፋ አደረገች
ሩሲያ ከአንድ ዓመት በፊት 147 ሺህ አዲ ወታደሮችን የመለመለች ሲሆን የሀገሪቱ አጠቃላይ ወታደሮች ብዛትም ወደ ሶስት ሚሊዮን ከፍ እንዲል የሚያደርግ ህግም አሳልፋለች፡፡
ከዩክሬን ጋር የተጀመረው ጦርነት ከተጀመረ ሶስተኛውን ዓመት የያዘ ሲሆን ጦርነቱ በየጊዜው መልኩን እየቀያየረ ይገኛል፡፡
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ከሰሞኑ የአሜሪካ ድጋፍ ከቆመ በሩሲያ እንሸነፋለን ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል፡፡
የአሜሪካ ሪፐብሊካን ምክር ቤት አባላት ለዩክሬን የሚሰጠው ድጋፍ መቃወማቸውን ተከትሎ የአውሮፓ ሀገራት ክፍተቱን ለመደገፍ የጦር መሳሪያ እና ሌሎች ድጋፎችን በማድረግ ላይ ናቸው፡፡