ኢኮኖሚ
የቻይናው የስልክ ቀፎ አምራቹ ሺዮሚ የተሰኘው ኩባንያ የኤሌክትሪክ መኪና ማምረት ጀመረ
ኩባንያው አንድ ዘመናዊ መኪናን በ69 ሺህ ዶላር ዋጋ ለገበያ አቅርቧል
ሺዮሚ ኩባንያ ከአፕል እና ሳምሰንግ በመቀጠል የዓለማችን ሶስተኛው ግዙፍ የሞባይል ስልክ አምራች ተቋም ነው
የቻይናው የስልክ ቀፎ አምራቹ ሺዮሚ የተሰኘው ኩባንያ የኤሌክትሪክ መኪና ማምረት ጀመረ።
የቻይና ኩባንያዎች የዓለም ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ገበያን የተቆጣጠሩ ሲሆን አሁን ደግሞ ሺዮሚ የተሰኘው የሞባይል ስልክ አምራች ኩባንያው ምርቱን አስተዋውቋል።
ኩባንያው ሱ7 የተሰኘውን ዘመናዊ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ለዓለም ገበያ ማቅረቡን አስታውቋል።
የኩባንያው ስራ አስፈጻሚ ሌ ጁን እንዳሉት ሽዮሚ ኩባንያ ከሞባይል ስልክ ባለፈ ሱ7 የተሰኘ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ በ69 ሺህ ዶላር ለዓለም ገበያ አቅርቧል ብለዋል።
ሺዮሚ የቴክኖሎጂ ኩባንያ በ2023 ዓመት በሽያጭ ብዛት ከዓለም ሶስተኛው ኩባንያው እንደሆነ የሮይተርስ ዘገባ ያስረዳል።
ኩባንያው አሁን ላይ ትኩረቱን ከሞባይል ስልክ በተጨማሪም ወደ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ማምረት ማድረጉን ሀላፊው ተናግረዋል።
ስራ አስፈጻሚው አክለውም ሺዮሚ ኩባንያ በቀጣዮቹ 10 ዓመታት ውስጥ 10 ቢሊዮን ዶላር በጀት መመደቡንም አስታውቀዋል።
አፕል ኩባንያ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ የማምረት እቅድ የነበረው ቢሆንም ይህንን እቅዱን ሰርዣለሁ ማለቱ ይታወሳል።